ዜና፡ ሲዳማ ክልል አጎራባች በሆነው በምዕራብ አርሲ ዞን ተከስቶ የነበረው ግጭት የግለሰቦች እንጂ በአጎራባች ህዝቦች መካከል አልነበረም ሲል የሲዳማ ክልል አስታወቀ

ፎቶ ከማህበራዊ ሚዲያ

አዲስ አበባ መጋቢት 2/ 2015 ዓ.ም፡– በርካታ መገናኛ ብዙሃን ለሲዳማ ክልል አዋሳኝ በሆነው የኦሮምያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ነሰቦ ወረዳ ቦጨሳ ቀበሌ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ግጭት ተከስቶ በርካታ ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል። በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየታቸው ለአዲስ ስታንዳርድ የሰጡን የሲዳማ ክልል የፍትህ እና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ግጭቱ በግለሰቦች መከካል የተፈጸመ እንጂ ከድንበርም ይሁን ከማንነት ጋር የተገናኘ አይደለም ብለዋል። በግጭቱ ሳቢያ የሰው ህይወት መጥፋቱን፣ ንብረት መውደሙን ያስታወቁት አቶ አለማየሁ ጉዳቱ በሁለቱም ህዝቦች ደርሷል ብለዋል። ግጭቱ የተፈጠረው የሲዳማ ብሔር ተወላጅ የሆነ ግለሰብ በምስራቅ ጉጂ ዞን በምትገኝ ጉቦ ቀበሌ በተፈጠረ ጠብ አንድ ግለሰብ በመግደሉ የገዳይ ቤተሰቦች የሆኑ የጉጂ ኦሮሞዎች የበቀል እርምጃ በመውሰዳቸው መሆኑን ገልጸዋል።

የሁለቱም ክልሎች የጸጥታ መዋቅር ተደራጅቶ ከአከባቢው የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ሁኖ እየሰራ መሆኑን የጠቀሙት ሃላፊው በሚቀጥለው ሳምንት የእርቀሰላም ኮንፈረንስ ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙን አስታውቀዋል።

አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ በተጨማሪም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ እንደተባለው የኦሮሞ ተስፋፊ ሀይል በሲዳማ ወረራ ፈጽሟል በሚል የሚነዛው ፍጹም ሀሰት ነው ሲሉ ገልጸው ይህም ሆን ተብሎ የኦሮሞ ህዝብ፣ መንግስትን እና የጸጥታ አካላትን ስማቸውን ለማጠልሸት መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ ብለዋል። የተዋጋ የኦሮምያ ሀይል የለም፣ የተዋጋ የሲዳማ ልዩ ሀይልም የለም ብለዋል።

የምዕራብ አርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አህመድ ሃጂ በአከባቢው የተከሰተው ግጭት መንስኤው ራሱ ምዕራብ አርሲ ዞን አይደለም ሲሉ ገልጸው ጉዳዩን ሲያብራሩም የሲዳማ ተወላጅ ወደ ምስራቅ ጉጂ ዞን ጉቦ በምትባል ቦታ በግለሰብ ግጭት ሰው ይገድላል፤ በዚህም የጉጂ ኦሮሞዎች የኛ ሰው ተገድሎብናል በሚል ገዳዩን ለመበቀል ወደ ምዕራብ አርሲ በመምጣት ግድያ ፈጽመዋል ሲሉ መንስኤውን ነግረውናል። በሌሎች ሚዲያዎች እንደተዘገበው ለስብሰባ ተጠርተው ጥቃት ተሰንዝሮባቸው ነው የተገደሉት የተባለው ሀሰት ነው ያሉት አስተዳዳሪው የኦሮሞ ጉጂዎች ናቸው ወደ አከባቢው በመሄድ ግጭቱን የፈጠሩት፤ እንዴት ሲዳማዎች የኛን ሰው ይገድሉብናል በሚል ነው ሲዳማዎች ላይ ጥቃት የፈጸሙት ብለዋል። የሰው ህይወት በሁለቱም ወገን ጠፍቷል፤ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አሉ፣ ንብረታቸው የተወሰደባቸውም አሉ ግን እንደሚወራው የተጋነነ አይደለም፤ ይህንንም በቦታው ተገኝተን ተረድተናል ብለዋል። በሰው ህይወት ስለደረሰው ጉዳት መጠን ተጠይቀው በመጣራት ላይ ሰለሆነ ቁጥሩን ለመናገር አልችልም ብለዋል።

በሁለቱም በኩም ሽማግሌዎች ተቀምጠው ተወያይተዋል፤ የእርቅ ቀን ቆርጠዋል ያሉት አስተዳዳሪው የተዘረፉ ንብረቶች በመመለስ ላይ እንደሚገኝ አስታውቀው ወደ 32 የሚጠጉ በሲዳማዎች በኩል የተዘረፉ መመለሳቸውን በአብነት ጠቅሰዋል።

በአከባቢው የሚገኙ ሰዎች በውሃም በሳርም ይጋጫሉ፤ የተለመደ ነው ያሉት አቶ መሃመድ ጉዳዮቹ በባህላዊ መንገድ ነው ሲፈቱ የኖሩት ብለዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.