አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19/2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሥራቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን በይፋ አስታውቁ፡፡
የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳ ብርቱካን ሚደቅሳ ጤናዬን በሚገባ ለመጠበቅ የረጅም ጊዜ እረፍት የሚያስፈልገኝ ሆኖ በመገኘቱ ከ ነሀሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቦርድ ሰብሳቢነቴ በገዛ ፍቃዴ መልቀቄን ለተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ጽህፈት ቤት ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም አሳውቄያለሁ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።
ሰብሳቢዋ ሥራ በሚቀራቸው ጊዜም ያልተጠናቀቁ ሥራዎችን የማጠናቀቅ እና አስተዳደራዊ ሽግግር ሥራዎችን ለመሥራት ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡም አስታውቀዋል፡፡
በ2011 ዓ.ም ታህሳስ ወር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ በመሆን ስራዬን ስጀመር ተቋማችንን ተአማኒ እና ራሱን ችሎ ምርጫን ማከናወን የሚችል ተቋም ለማድረግ በማለም ነበር ያሉት ሰብሳቢዋ “ባለፉት አራት አመት ከስድስት ወራት ሶስት ህዝበ ውሳኔዎችን እና አገራዊ ምርጫን በማካሄድ እና ፓለቲካ ፓርቲዎችን በማስተዳደር የተሰጡኝን ሃላፊነቶች ህጋዊነት ፍትሀዊነት እና ቅንነትን በተከተለ ሁኔታ ለማከናወን ስጥር ቆይቻለሁ” ብለዋል።
በመጨረሻም ቦርዱን በሰብሳቢነት ለመምራት በእጩነት ላቀረቧቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዲሁም እምነቱን ጥሎ ሀላፊነቱን ለሰጣቸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምስጋና አቀርበዋል፡፡ አስ