ዕለታዊ ዜና፦የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እና የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መረጃን ለማጋራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረራሙ


ሃምሌ 13፣ 2014 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፦የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ እና የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና  በቴክኖሎጂ አማካኝነት መረጃን ለማጋራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረራሙ፡፡

ሁለቱ መስሪያ ቤቶች የተፈራረሙት ስምምነቱ የአቅም ግንባታ እና የቴክኖሎጂ እገዛ ሲሆን አጠቃላይ በዚህ ዓመት አምስት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ መፈራረማቸው ነው የተገለፀው።

ዶክተር ለገሰ ቱሉ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ዘመኑ የሚፈልገውን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥራ ለመሥራት መረጃን በተቀላጠፈ እና በተሻለ ትንተና ወደ ማህበረሰቡ እንዲደርስ ለማድረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በሰው ሰራሽ አስተውህሎ መታገዙ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ይህን ለማሳካትም ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር ለመስራት ስምምነት መደረሱን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቼና በበኩላቸው የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለሕዝብ ተደራሽ የሚያደርጋቸውን መረጃዎች በተቀላጠፈና በተተነተነ መንገድ ተደራሽ ለማድረግ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ድጋፍ ያእንደሚያደርግ ገልጸዋል። አክለውም መረጃ በማሰባሰብ እንዲሁም በመተንተን እና ተደራሽ በማድረግ በቴክኖሎጂ ለማገዝ ተቋሙ ዝግጁ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.