ትንታኔ፡- የሰላም ድርድሩ የተስፋ ጭላንጭል ያሳያቸው ከአመት በላይ ተለያይተው የነበሩ የትግራይ ቤተሰቦች ጉጉት

አለማቀፍ የቀይ መስቀል ማህበር በኮሙዩኒኬሽን መቋረጥ ምክንያት የተለያዩ የትግራይ ቤተሰቦችን ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር የማገናኘት ሙከራ። ፎቶ፡ አለማቀፍ የቀይ መስቀል ማህበር

በምህረት ገ/ክርስቶስ @MercyG_kirstos

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29/2015 ዓ.ም፡- ሰኔ 2013 ዓ/ም በትግራይ ክልል ባለስልጣናት እና በፌዴራል መንግስት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ በተነሳው ጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል የስልክ፣ የኢንተርኔት፣ የመብራትና የባንክ አገልግሎቶች ለሁለት ዓመታት ተቋርጦ ቆይቷል።

ከእነዚህ አገልግሎቶች በተጨማሪ የአየር እና የምድር ትራንስፖርት በመቋረጡ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች እንደዚሁም በስራ ምክንያት ወደ ትግራይ ሄደው ወይም ከትግራይ ክልል ወደ ሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች ወጥተው የነበሩ ዜጎች ከቤተሰቦቻው እና ከዘመዶቻቸው ጋር አንዲለያዩ ምክንያት ሁኗል።

በተለያዩ የውጭ ሃገራት የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችም ትግራይ ውስጥ ከሚኖሩ በስልክም ሆነ በሌላ ዘዴ መገናኘት ባለመቻላቸው የቤተሰቦቻቸውን ደህንነት ማወቅ አለመቻላቸውን በተለያየ መንገድ ስገልጹ ቆይተዋል።

የ30 ዓመት ወጣቱ ክፍሎም (ስሙ ለደህንነት ሲባል ተቀይሯል) መኖሪያቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጅ አንዱ ነው። ቤተሰቦቹ ትግራይ ዓዲግራት ከተማ አቅራቢያ በሚትግኝ የገጠር ከተማ እንደሚኖሩ ይናገራል።

የቤተሰቦቹ በህይወት መኖር እና አለመኖ ባለማወቁ ምክንያት ለጭንቀት እንደተዳረገ ክብሮም ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግሯል።

የመገናኛ መንገዶች ሙሉ በሙሉ ከመቋረጡ በፊት እናቱን በሳምንት ቢያንስ አራት ጊዜ በስልክ ያነጋግራቸው አንደነበር የገልጸው ክብሮም ችግሩ ከተከሰተ አንስቶ እስካሁን ግን ደህንነታቸውን ማወቅ አልቻለም።

“ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ አባቴ አንድ ግዜ ኔትወርክ ይሰራ ወደነበረበት ተራራ ሄደው በስልክ ሊያነጋግሩት የሞክሩ ቢሆንም በኔትወርኩ መቆራረጥ ምክንያት መደማመጥ አንዳልቻሉና ቆይቶም ሙሉ በሙሉ መቆራርጡን ይገልጻል” ይላል።

ከብሮም ሽያይዞመ ለመጨረሻ ግዜ ቤተሰቦቹን በስልክ ያገኘው ጦርነቱ ከተጀመረበት ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓም ሁለት ሳምንት በፊት እንደሆነ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግሯል።

አንዳንድ በትግርራይ የተለያዩ አከባቢዎች የሚኖሩ ግለሰቦች ወደ ኮረምና አላማጣ እንደዚሁም ወደ ሌሎች የትግራይ አካባቢዎች እየሄዱ የሚደውሉ ቢሆንም የትራንስፖርት ክፊያው ከአቅም በላይ በመሆኑ ሁሉም ሰዎች ማድረግ አልቻሉም።

ከዚህም በተጨማሪ የተቀዳ የድምፅ መልዕክቶችን በመላክ ለዘመዶቻቸው በሰላም መኖራቸውን ያሳውቁ ነበር። ይህንንም ቢሆን ከአንዳንድ የግብረሰናይ ድርጅቶች ሰራተኞች የሚያገኙት ውስን የኢንተርኔትና የሳተላይት አገልግሎት በመጠቀም ነበር።

“ለብቻቸው የሚኖሩ ህጻናት ያልተጠበቀ ስቃይና መከራ የደረሰባቸው ሲሆን ሚያስፈልጋቸው አንክብካቤና ጥበቃ ላይደርግላቸው ይችላል”።

አለማቀፍ የቀይ መስቀል ማህበር

አለማቀፍ የቀይ መስቀል ማህበር በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተሰቦች በሌላ አካባቢ ካሉ ቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ ባደረገው ጥረት ከጥር 2014 ዓም ጀምሮ በዘጠኝ ተከታታይ ወራት ከ 185 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ነፃ የስልክ ጥሪዎች እና የጽሑፍ መልዕክቶች እንዲገናኙ ማደረጉን አስታውቋል።

በክልሉ በተቋረጠው የግንኙነት መስመር ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸው ቤተሰቦች ከመለያየታቸውም በላይ የክልሉ ህዝብ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች በአጅጉ አንዲጎዳ አድርጎታል።

እንደ ዓለማቀፍ ቀይ መስቀል ከሆነ ቤተሰቦች በሰብአዊ ቀውስ ውስጥ አንዱ የሌላውን መኖር እና አለመኖር በማያውቅበት ሆኔታ የትግራይ ተወላጆች ቀላል የማይባል ፍርሃትና ድንጋጤ አንዲፈጠርባቸው በማድረጉ የትግራይ ተወላጆች የሥነልቦናዊና የጤና መጓደልን ችግሮች ሊያስከትልባቸው እንደሚችል ገልጾ ነበር።

ዓለም አቀፍ ቀይመስቀል አያይዞም በተለይም “ለብቻቸው የሚኖሩ ህጻናት ያልተጠበቀ ስቃይና መከራ የደረሰባቸው ሲሆን ሚያስፈልጋቸው አንክብካቤና ጥበቃ ላይደርግላቸው ይችላል”።

በሐምሌ ወር በአሜሪካ ኦሪጎን በተካሄደው 18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች ማራቶን ላይ በመሳተፍ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነችው አትሌት ጎቲቶም ገብረስላሴ ደስታዋን ከቤተሰቦቿ ጋር መጋራት አልቻለችም ነበር።

እናቷ ወይዘሮ በረኺቱ ካሳ የሚኖሩት በትግራይ ክልል በመሆኑና በክልሉ ምንም ዓይነት የመገናኛ ዘዴ ባለመኖሩ የተነሳ እናት እና ልጅ መገናኘት አንዳልቻሉ በወቅቱ መገለጹ የሚታወስ ነው።

“የልጄ ነገር በጣም ያሳስበኝ ነበር እሷም በፊናዋ ስትጨነቅ ነበር። ሆኖም ግን ከሰባት ወራት በፊት ወደ አላማጣ ሄጄ በስልክ አገኛኋት። ከዚያ በኋላ ግን እኔ ማድረግ የቻልኩት በሰዎች በኩል የድምጽ መልእክት መላክ ስለነበር እንዳትጨነቅ ይህንኑ አደርግ ነበር” ሲሉ ተናግረዋል።

ክፍሎም በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ድርጅት ተቀጥሮ የሚሰራ ሲሆን የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ቤተሰቦቹን ያስተዳድር እንደነበር ያስታውሳል። “ሰላም እያለ ለእናቴ ገንዘብ እልክላት ነበር ባለፉት ሁለት ዓመታት ግን የባንክ አገልግሎት በመዘጋቱ ምክንያት ለእናቴም ሆነ ለሌች ቤተሰቦቸ መርዳት አልቻልኩም፣ ከዚያም በላይ በህይወት ይኑሩ አይኑሩ ምንም የማቀው ነገር የለም” ብሏል።

“ሁሉም ነገር በመዘጋጋቱ ምክንያት ሰላም ያለው ህይወት እንዳልመራ አድርጎኛል እያደረግኩ ባለሁት የዕለት ተለት እንቅስቃሴ ላይም ከፍተኘዓ ተጽእኖ አሳድሮብኛል፤ በሙሉ ልብና አቅም መሥራት አልቻልኩም። ከሁሉም በላይ ደግሞ ከፍተኛ ጭንቀት ፈጥሮብኛል፤ ሁልጊዜ ስለ ቤተሰቦቼ መኖርና አለመኖር አስባለሁ። ህይወቴን በአሳዛኝ መንገድ ነው አየመራሁት ያለሁት። በሰላሙ ግዜ ከቤተሰቦቼ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እወያይ ነበር እነሱም ያማክሩኝ ነበር ይህ ሁሉ ነገር አሁን የለም”።፣

በትግራይ ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በየቀኑ የቀይ መስቀልን በር ያንኳኩሉ አንዲሁም በአካባቢው ከተገኙ ጥቂት የሳተላይት ስልኮች ቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት ወረፋ ይጠብቃሉ።

ከአለም አቀፍ የቀይ መስቀል ማህበር የተገኘ አጭር ቪድዮ አንደሚያሳየው ከሆነ ሰዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር በሳተላይት ስልክ ተነጋግረው በናፍቆት ሲያለቅሱ እና ስበደስቱ አንዳንዶቹ ደግሞ የወዳጅ ዘመዶቻቸውን ድምጽ ከሰሙ ቡኃላ የአእምሮ ሰላም ሲያገኙ ይስተዋላል። በሌላ በኩል ደሞ የሃዘን ወይም አስደንጋጭ ዜና ሲሰሙ በኃዘን የሚጮሁና የሚደነጉጥም በርካቶች ናቸው።

“የቤተሰቦቼ ድህንነትና ጤንነታት በአጅጉ አሳስቦኛል፤ አዲስ አዲስ የዓለሁት እኔ ብቻ ነኝ። ወላጆቼም ሆኑ ስድስት ወንድሞቼ እህቶቼ ያሉት ትግራይ ነው”

ክፍሎም

ይህ አገልግሎት ግን ተደራሸ አይደለም። የቀይ መስቀል ማእከላት በሚገኙባቸው ቦታዎች አካባቢ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ናቸው በወረፋ ሲደርሳቸው ተጠቃሚ የሚሆኑት። በዚህ ምክንያት ቤተሰቦቹን በቀይ መስቀል አገልግሎት ሰጪ ተቋም እንዳላገኘ ክፍሎም ይናገራል።

“የቤተሰቦቼ ድህንነትና ጤንነታት በአጅጉ አሳስቦኛል፤ አዲስ አዲስ የዓለሁት እኔ ብቻ ነኝ። ወላጆቼም ሆኑ ስድስት ወንድሞቼ እህቶቼ ያሉት ትግራይ ነው። ምን አይነት ችግር አየገጠማቸው አንዳለ በመገመትም ያለእረፍት ስለነሱ እንዳስብ ተገድጃለሁ”።

መሰረት በርሀም የክፍሎም ሃሳብ ይጋራለች። እሱም በአንድ የግል ድርጅት ተቀጥሮ ይሰራል። ጦርነቱ ከመቀስቀሱ አከንድ ሳምንት በፊት ለስልጠና ነበር ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ የመጣው። በጦርነቱ መጀመርና አገልግሎቶች መቋረጥ ምክንያት ወደ ቤተሰቦቹ መመለስ አንዳልቻለ ይናገራል።

“ጦርነት ከመጀመሩ ከአንድ ሳምንት በፊት የመጣሁ ሲሆን መመለስ ባለመቻሌ እዚህ ያገኘሁትን ስራ መስራት ጀመርኩ” ይላል መሰረት።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የበአዲስ አበባ ነዋሪና የሁለት ልጆች አባት የሆኑ የትግራይ ተወላጅ እንዳሉት ደግሞ እንዳሉት ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ መቐለ ከሚገኙ ልጆቻቸው ጋር መገናኘት አንዳልቻሉና ልጆቻው በምን ሁኔታ ውስጥ አንዳሉ አንደማይዋቁ ይናገራሉ።

“በስምምነቱ ከማንም በላይ ደስተኛ ነኝ። በፍጥነት መሬት ላይ ቢተገበር ቤተሰቦቼን በረሃብ እና በመድሃኒት እጦት ከመሞት ይታደጋቸዋል”

መሰረት

አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው ሶስቱም የትግራይ ክልል ተወላጆች ባለፈው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት እና የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት በጣም ጥሩ ተስፋ አንደሆነ ተናግረዋል።

“በስምምነቱ ከማንም በላይ ደስተኛ ነኝ። በፍጥነት መሬት ላይ ቢተገበር ቤተሰቦቼን በረሃብ እና በመድሃኒት እጦት ከመሞት ይታደጋቸዋል” ይላል መሰረት።

የቤተሰቦቸን ሁኔታ ለማወቅ በጣም ጓጉቻለሁ ያለው መሰረት ስምምነቱ ከተሳካ ወደ ቤተሰቦቸም ሆነ ወደ ሙያዬ ለመመለስ ትልቅ ተስፋ ነው ይላል።

ነገር ግን ምንም እንኳን ስምምነቱ ቢኖርም “ጦርነቱ አሁንም ሊቀጥል ይችላል” የሚል ስጋት እንዳደረበት በመግለጽ ተፋላሚ ወገኖች “በራሳቸው የፖለቲካ ፍላጎት ላይ ከማተኮር” ይልቅ ለሲቪሎች ቅድሚያ እንዲሰጡ አሳስቧል.

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቀው ግለሰብ “በሰላም ስምምነቱ በጣም ተደስቻለሁ፣ ልጆቼ በጣም ናፍቀውኛል እነሱን ለማግኘት ተስፋ ላይ ነኝ ብሏል። “ሁለቱም ወገኖች በጥሩ ሁኔታ ወስነዋል ነገር ግን የውጭ ተፋላሚ አካል በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረገውን ስምምነት ሊረብሽ ይችላል የሚል ስጋት አለኝ” ሲል አክሏል።

በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ከብዙ ጥረትና ሚስጥራዊ ስብሰባ በኋላ በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሓት መካከል ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ/ም የተደረገው ዘላቂ የቶክስ ማቆም ስምምነት እንደሚደግፉ አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው የትግራይ ተወላጆች ተናግረዋል።

ምንም እንኳን አፈጻጸሙ ላይ ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮች ባይካተቱም በትግራይ የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎን ጨምሮ የተቋረጡ አገልግሎቶች ወደነበሩበት ሊመለሱ መሆኑን የሁለቱ ወገኖች የጋራ መግለጫ አመልክቷል።

ይህ በጦርነቱ ለተጎዱ ሰዎች አዲስ ተስፋ ሰጥታቸዋል። አንዲሁም በጦርነቱ ለተጎዱት የማህበረሰብ አካላትና ለረጀም ግዜ ከቤተሰቦቻቸው ተለያይቶ ለነበሩ ዜጎች ትልቅ ተስፋ መሆኑን ክፍሎም ይናገራል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.