ዜና ፡- የኢትዮጵያ መንግስት ከሌሎች ታጠቂ ኃይሎች ጋርም ሰላማዊ ድርድር እንዲደርግ ኢዜማ ጠየቀ ፣ በትግራይ የሚገኙ ፓርቲዎች በበኩላቸወ ስምምነቱ የትግራይ ህዝብ የፈጠረውን አቅም የሚያመክን መሆኑን አስታወቁ
አዲስ አበባ፣ጥቅምት25/ 2015 ዓ.ም፡- በኢትዮጵያ መንግስት እና በትግራይ አመራሮች መካከል የተደረገው ስምምነት “መርህ የተከተለ” መሆኑን በመጥቀስ በተመሳሳይ መልኩ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ከሚገኙ ሌሎች ታጠቂ ኃይሎች ጋርም ሰላማዊ ድርድር በማድረግ ሰላማዊ መፍትሄ መፈለግ ተገቢ መሆኑን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አስታወቀ፡፡ ኢዜማ የኢትጵያ መንግስትና የህወሓት ባለስልጣናት የተፈራረሙት