ዜና፡ የኢትዮጵያ መንግስት ሂዩማን ራይትስ ዎች በምዕራብ ትግራይ የሚካሄደው የዘር ማጽዳት ወንጀል ቀጥሏል በማለት ያወጣውን ሪፖርት እንደማይቀበለው ገለፀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2015፡- የኢትዮጵያ መንግስት ሂዩማን ራይትስ ዎች በምዕራብ ትግራይ የሚካሄደው የዘር ማጽዳት ወንጀል እንደቀጠለ ነው በማለት ያወጣውን ሪፖርት እንደማይቀበለው አስታወቀ፡፡ በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል የሰላም ስምምነት ቢፈረምም አሁንም በምዕራብ ትግራይ የሚካሄደው የዘር ማጽዳት የወንጀል ተግባር መቀጠሉንና የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላትም