ዜና፡ የቀድሞ የጤና ቢሮ ከፍተኛ ባለስልጣን በጥላቻ ንግግር ተጠርጥሮ በሶማሊ ክልል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ
አቶ ሲራጅ አደም ፎቶ፡ ጓደኛው አዲስ አበባ፣ ህዳር 10/2015 ዓ.ም: – የቀድሞው የሶማሊ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ ሲራጅ አደም ሐሙስ ህዳር 9 ቀን 2015 ዓ/ም በድሬዳዋ ከተማ ተይዞ ወደ ሶማሊ ክልል መዲና ጅግጅጋ ከተማ ተወስደው በእስር ላይ አንደሚገኙ ለአዲስ ስታንዳርድ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል። የቀድሞ የሶማሊ ክልል የጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ ሲራጅ አደም በ2013 ዓ/ም ከስልጣናቸው ከለቀቁ በኋላ የመንግስት ተቺ በመሆን በተለያዩ ማህበራዊ