ዜና ትንተና: በ3 ቀናት ውስጥ ብቻ 10 የጋዜጠኞች፣ የማኅበረሰብ አንቂዎች ባህር ዳር እና አዲስአበባ ላይ ታስረዋል
በማህሌት ፋሲል አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16/2014:- ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በሦስት ቀናት ውስጥ በአጠቃላይ 10 ጋዜጠኞች እና የሚዲያ አካላት መታሰራቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል። በቁጥጥር ስር የዋሉት በአማራ ክልል ርዕሰ መዲና ባህር ዳር እና አዲስ አበባ መሆኑን መገናኛ ብዙሀኑ እና ከእስረኞቹ ቤተሰቦች የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ አየር መንገድ