ዜና፡ ቤተክርስቲያኗ የዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሰጠች፤ በትግራይ አባ ሰረቀብርሃንን ጨምሮ አስር አባቶች ለኤጲስ ቆጶስነት መመረጣቸው ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በኦሮምያ እና በደቡብ ክልል ለሚገኙ ሀገረ ስብከቶች የሚመደቡ የዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት መስጠቷ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ለዘጠኙ ኤፒስ ቆጶሳት ሹመቱን የሰጡት በመንበረ ፓትሪያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም መሆኑን ታውቋል።