እለታዊ ዜና፡ በመዲናዋ ከፍተኛ የውሀ እጥረት መከሰቱን የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ


ምስል- አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11/2014 ዓ.ም፡- በአቃቂ ከርሰ ምድር የውኃ ፕሮጀክት ውስጥ የሚገኙ አምስት የውኃ ጉድጓዶች በጎርፍና ደለል በመሞላታቸው ምክንያት በመዲናዋ  ከፍተኛ የውኃ እጥረት መከሰቱን የአዲስ አበባ ከተማ ውኃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን  አስታወቀ።

ባለስልጣኑ በቀን 20 ሺሕ ሜትር ኪዮብ ውኃ የማምረት አቅም ያላቸው አምስቱ የውኃ ጉድጓዶች ንፋስ ስልክና ቂርቆስ ክ/ከተሞችን ጨምሮ በርካታ የከተማዋን አካባቢዎች የሚሸፍኑ ሲሆን አሁን ሙሉ በሙሉ ማምረት አቁመዋል ብሏል። በዘንድሮው የክረምት ወቅት ከመደበኛው በላይ የጎርፍ ፍሰት በመኖሩ ምክንያት የውኃ ጉድጓዶችን ከመሰል ችግሮች ለመጠበቅ በተሰራው የመከላከያ ግንብ መቆጣጠር እንዳልተቻለ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል

የውኃ እጥረቱን በጊዜያዊነት ለመቅረፍ በሳምንት ሁለት ወይም ሶስት ቀን ውኃ ያገኙ ከነበሩ አካባቢዎች በመቀነስ እጥረቱ ወደተከሰተባቸው አካባቢዎች እየተላከ እንደሆነ ተገልጿል። የተፈጠረው ወቅታዊ ችግር እስኪፈታ ድረስ የከተማዋ ነዋሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ  ባለስልጣኑ ጥሪ አቅርቧል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.