ፈጠራ፦ የገጠር እና የሩቅ አካባቢ ተማሪዎችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለማድረግ ያቀደው “ዲጂ ትራክ” ኢትዮጵያ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ

ቤተልሔም ደሴ፣ የ’ICog Anyone Can Code’ ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ ሊዮ ሊዩ፣ የሁዋዌ ሰሜን አፍሪካ ሪጅን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)፣ የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ እና ፍፁም አሰፋ፣ የኢትዮጵያ የዕቅድና ልማት ሚኒስቴር።

“DigiTruck ” ተንቀሳቃሽ ዲጂታል መማሪያ ክፍል ሲሆን ከገጠር አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስልጠና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል።

አዲስአበባ፣ህዳር 08/2015 ዓ.ም. ፦ የሁዋዌ ፕሮጀክት የሆነው ዲጂ ትራክ ከኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር እና ከ’ICog Anyone Can Code’ ( ICOG ACC) ጋር በመተባበር የገጠር እና የሩቅ አካባቢ ተማሪዎችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለማድረግ በማሰብ በኢትዮጵያ በይፋ ተመርቋል።

ዲጂ ትራክ ኢትዮጵያ የላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን፣ ሮቦቲክ መሳሪያዎችን እና ማይክሮ ኤሌክትሮኒክስን ጨምሮ የተማሪዎችን የመማር ማስተማር ሂደት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚያደርሱ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች የተገጠመለት ተንቀሳቃሽ የስልጠና ማዕከል በመሆን የሚያገለግል 40ft ኮንቴነር ሲሆን በስልጠናው በመላው ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ዙር የተመረጡ ከተሞች ስልጠና ይሰጣል፡፡ በስልጠናውም ተማሪዎች ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና፣ አርት እና ሂሳብ “STEAM” ትምህርት ፋይዳ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ይሰራል፡፡

የዲጂትራክ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ከኮምፒዩተር፣ ከፕሮግራሚንግ፣ ከኢንተርኔት ዘርፎች(IOT) እና ሌሎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋር እንዲተዋወቁ የሚያስችል ማዕቀፍ በማዘጋጀት የዲጂታል ክፍፍልን ለማጥበብ የሚሰራ ነው፡፡ ፕሮጀከቱ በመላው ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለመከታተል ከቴክኖሎጂ ጋር የተገናኙ ክህሎቶችን ሊታጠቁ እንደሚገባ ያምናል፡፡

በዚህም መሰረት የሁዋዌ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር እና የምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው የግል አርተፊሽያል ኢንተለጀንስ እና የሮቦቲክስ ምርምር እና ልማት የግል ኩባንያ ጋር በመተባበር የሙከራ ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድረግ እና የስልጠና ፕሮግራሙን በመላ ሀገሪቱ ለማስጀመር ችሏል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የሁዋዌ ኖርዘን አፍሪካ ሪጅን ምክትል ፕሬዚዳንት ሊዮ ሊዩ “ሁዋዌ ኢትዮጵያ ከዋና ፕሮጀክቶቹ አንዱን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣቱ ደስተኛ ነው። ድርጅታችን በኢትዮጵያ ጠንካራ የአይቲ ተሰጥኦ ምህዳር ለመገንባት ምንጊዜም ቁርጠኛ ነው። ከሁዋዌ ቴክ 4ኦል ዋና ዋና ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነውን ዲጂ ትራክን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣታችን ደስተኞች ነን። ይህ በእንዲህ እንዳለ ታዳጊ ልጆች ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ እና በዲጂ ትራክ በኩል የዲጂታል ቴክኖሎጂን እንዲያገኙ ማስቻል የሁዋዌ ፍላጎት ነው” ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲተገበር ተማሪዎች የተለያዩ ትምህርቶችን ለመማር ያላቸውን አመለካከት፣ ከሂሳዊ አስተሳሰብ ችሎታቸው ጋር አብሮ ያሻሽላል ተብሎ ይጠበቃል፣ ይህም በተማሪዎች ትምህርት አቀባበል ከፍተኛ አፈፃፀም ያስገኛል ። ፕሮጀክቱ የተማሪዎችን ተነሳሽነት፣ ትኩረት፣ የግንዛቤ ሂደት፣ የማንበብ ግንዛቤን፣ ሂሳዊ አስተሳሰብን እና ፈጠራን በእጅጉ ያሳድጋል። የተነደፈው መርሃ ግብር ተማሪዎችን ከመደበኛ የትምህርት እውቀታቸው ባሻገር፣ እንደ ቴክኖሎጂ እውቀት፣ መረጃ አስተዳደር፣ ግንኙነት፣ የቡድን ስራ፣ ስራ ፈጠራ፣ አለምአቀፍ ግንዛቤ፣ የሲቪክ ተሳትፎ እና ችግር ፈቺ እንዲሁም እንደ ሮቦቲክስ ያሉ የቴክኖሎጂ ችሎታዎችን ማዳበር ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) እንደገለፁት “የሁዋዌ ዲጂ ትራክ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ከ’Icog Anyone Can Code’ ጋር በመተባበር የልጆቻችንን እና የወጣቶችን እውቀት እጅግ በጣም መሠረታዊ በሆነው በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ላይ ለማዳበር ከተዘጋጁት ውጥኖች አንዱ ነው ። በዚህም መሰረት ከአንድ አመት ዝግጅት በኋላ የትምህርት ሚኒስቴር፣ ሁዋዌ እና አይኮግ በመተባበር የዲጂ ትራክ ኢትዮጵያ ፕሮጀክትን በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ አድርገዋል። በዲጂትራክ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በተቻለ መጠን የዲጂታል ቴክኖሎጂን ጥቅም ማግኘት እንደሚችሉ እና የዲጂታል ቴክኖሎጂን ልምድ በሚያስደንቅ ሁኔታ እንደሚያዳብሩ ተስፋ ተጥሏል” ብለዋል።

የ’Icog Anyone Can Code’ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቤተልሔም ደሴ በበኩላቸው “ ይህን ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ ሳስብ እኔ በልጅነቴ ያገኘሁትን ዕድል ለሌሎች ለመስጠት ለመሞከር ነው። የ 21 ኛው ክፍለ ዘመን መሰረታዊ ችሎታዎች መግቢያ የሆነውን የቴክኖሎጂ ትምህርት ዛሬ ለወጣቶች በጣም አስፈላጊ መሆኑን አምናለሁ፣ ይህም እድ

ለወጣቶች የሚፈጥረው የእውቀት ነፃነት ትልቅ ነው። ዲጂትራክ ቀጣዩን ኮድ አድራጊ ትውልድ በማነሳሳት የአገሪቱን የቴክኖሎጂ ስነ-ምህዳር የወደፊት እጣ ፈንታ የሚቀርፁ የፈጠራ ባለሙያዎችን መረብ እየገነባ ነው። ይህ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ዙሪያ ያሉ ህፃናትን እና ወጣቶችን በዲጂታል እውቀት ለማሳደግ እና በሮቦቲክስ ላይ ለማስተማር በምናደርገው ጥረት ውስጥ ትልቅ ድርሻ ይይዛል።” ሲሉ ተናግረዋል።

ዲጂትትራክ ኢትዮጵያ ሴት ተማሪዎችን በቴክኖሎጂ ትምህርቶች ላይ ያላቸውን ፍላጎት ለማሳደግ አቅዶ የሚሰራ ሲሆን በ’STEAM’ ትምህርት ላይ በራስ መተማመን እንዲፈጥሩ እና ፍላጎቶቻቸውን እንዲያገኙ በሚያስችሉ ተግባራት በመሳተፍ በዘርፉ ያለውን የፆታ ተሳትፎ በማጥበብ ረገድ ያግዛል።

ፕሮጀክቱ ለሚቀጥሉት ሰባት አመታት የኮዲንግ ጉዞውን የሚቀጥል ሲሆን በተለያዩ የዞን ከተሞች ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ ከአጋር ድርጅቶች እና ከሚመለከታቸው የትምህርት ተቋማት ጋር በመሆን በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የተለያዩ ከተሞችን ለማዳረስ እቅድ ይዟል።

የዲጂ ትራክ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለው ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመመስረት የሚያስችል የቴክኖሎጂ ትምህርት ዘርፍ፣ የመጀመሪያ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና የዲጂታል ክህሎትን በመደገፍ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራ እና የህብረተሰብ መሻሻል ላይ ተጽዕኖውን ያሳድራል።

በማስጀመሪያ ዝግጅቱ የፕላን ሚኒስትር ፍጹም አደላን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.