ጥልቅ ትንታኔ፡ ከአማራ ክልል የሚመጡ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በሺዎች የሚቆጠሩ የምዕራብ ኦሮሚያ ነዋሪዎችን አፈናቀሉ

በአማራ ታጣቂዎች ጥቃት ከምዕራብ ኦሮሚያ የተፈናቀሉ የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት በአዳማ ከተማ ተጠልለው

በእቴነሽ አበራ @EteneshAB እና ደረጄ ጎንፋ @DerejeGonfa

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15፤2014-በምስራቅ እና በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች እየተካሄደ ያለው የእርስ በእርስ ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እያፈናቀለ ይገኛል፡፡ ለአዲስ እስታንዳርድ ተደጋጋሚ ቅሬታዎች ከሁለቱም ዞኖች ሲደርሳት ቆይተዋል፡፡ በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉ የምስራቅ ወለጋ ነዋሪዎች በነሱ አገላላፅ ‘ አማርኛ ተናጋሪ’ የታጠቁ ሀይሎች ጥቃት ምክንያት ከአካባቢያቸው ሲፈናቀሉ የአካባቢው አስተዳደር በበኩሉ የአካባቢው ፀጥታ አንዲሁም ጥቃቱን የፈፀሙ ሃይሎች በቦታው አለመኖራቸው ሳይረጋጋገጥ  ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እያስገደዷቸው መሆኑ ቅሬታ ፈጥሮባቸዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በሆሮ ጉዱሩ ዞን የምትገኘው አቤ ዶንጊሮ ወረዳ ነዋሪዎች ‘በፅንፈኛ የአማራ ታጣቂዎች’ አማካኝነት  ቅዳሜ የካቲት 5. 2014 ዓ.ም በደረሰው ጥቃት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ 30 ሰዎች መገደላቸውን ለአዲስ አስታንዳርድ በስልክ ገልፀዋል፡፡

ሆሮ ጉድሩ ዞን

እንደ ነዋሪዎች ገለፃ የአማራ ታጣቂ ሀይሎች ጥቃቱን ያደረሱት በአቤ ዶንጎሮ ወረዳ ውስጥ በምትገኘው ቦቶራ ቦራ ቀበሌ ሲሆን ቀኑም የካቲት 6፤ 2014 ነበር፡፡ በጥቃቱም 29 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን  ዝርፊያን ጨምሮ  ከ 64 በላይ ቤቶችን በእሳት ወድመው ነበር፡፡ ስሙ እንደይገለፅ የፈለገ የአቤ ደንጎሮ ነዋሪ ለአዲስ እስታንዳርድ በስልክ  “የአማራ ሚሊሻዎች ከአቤ ዶንጎሮ እና ጀርጋዳ ጃርቴ ወረዳ መጥተው ያለምንም ምህረት ከ20 በላይ ሰዎችን ህፃናትን እና ሴቶችን ጨምሮ ገድለው ሄደዋል” በሏል።

እንደ እማኙ ገለጻ ከሆነ የታጣቂዎቹ ሁለት አባላት በመጥፋቸው  እነሱን ለመፈለግ ታጣዊዎቹ መሰባሰብ እንደጀመሩ ተናግሮ “እነሱ በለሊት ሲመጡ ተኝተን ነበር ወዲያው ተኩስ ከፍተው ያገኙትን ሁሉ መግደል ጀመሩ።  ቤቶች ውስጥ ሰው እያለ እላያቸው ላይ እሳት መለኮስ ጀመሩ፡፡ የቻልነው ሮጠን አመለጥን ነገር ግን ያላመለጡት እዛው በእሳት ተቃጥለው ሞቱ” በማለት አብራርቷል፡፡ 

ምስክሩ ከሰጡት ገለፃ እሬሳቸው በአካባቢው ከተገኙ ሰዎች በተጨማሪ  ብዙ ሰዎች እሳከሁን የት እንደገቡ እንደማይታወቅ እና ቁጥራቸው የበዛ ወጣት ሴቶች በጉልበት ተጠልፈው  እንደተወሰዱ ለማወቅ ተችሏል።  

ምስክሩ ከሰጡት ገለፃ እሬሳቸው በአካባቢው ከተገኙ ሰዎች በተጨማሪ  ብዙ ሰዎች እሳከሁን የት እንደገቡ እንደማይታወቅ እና ቁጥራቸው የበዛ ወጣት ሴቶች በጉልበት ተጠልፈው  እንደተወሰዱ ለማወቅ ተችሏል።  

ሌላው ከጥቃቱ የተረፈ የወረዳው ነዋሪ በበኩሉ “ከእንቅልፌ የነቃሁት በተኩስ ድምፅ ነው። በሰዓቱ ቤቶች እየተቃጠሉ ስለነበር ሁሉም ህይወቱን ለማዳን ሩጫ ላይ ነበረ እኔም ቤተሰቦቼን ይዤ ሸሸሁኝ ፡፡ ” ጨምሮም “ቤቴ ከነሙሉ ንብረት እዛው ሲወድም የነበሩኝ 16 ከብቶች በጠቅላላ ተዘርፈዋል፡፡” ብሏል። የአይን ምስክሩ እንዳብራሩት አብዛኛዎቹ ተጎጂዎች ህፃናት፣ ሴቶች እና አረጋዊያን ናቸው፡፡ “19 ሰዎችን ከቀበርን በኋላ ሁለት አስክሬን አግኝተናል፡፡ ሌላ ቦታ ደግሞ 9 የሰው ጭንቅላት ለብቻ መገኘቱን ሰምቻለሁኝ፡፡”  ሲሉ ተደምጠዋል።

በሌላ በኩል ከጥቃቱ በማምለጥ ተደብቆ ከሚገኝበት ቦታ ለአዲስ ስታንዳርድ በስልክ የተናገረው ምስክር “አሁን ላይ የምንለምነው የፀጥታ ሀይሎች መጥተው እንዲያደኑን ነው፡፡ ምንም እንኳን ቤታችን ቢቃጠልም የተዘረፍነው ንብረታችን ተመልሶልን በድንኳንም ቢሆን ተመልሰን እንኖራለን። አጥቂዎቻችንም በህግ አንዲጠየቁ እንፈልጋለን” ብሏል።

ከምዕራብ ኦሮሚያ የተፈናቀሉ የሚያጠቡ እናቶች በአዳማ ከተማ በጋንዳ ኩርፋ አካባቢ ተጠልለዋል

እንደ ነዋሪዎቹ ገለፃ የአካባቢው አስተዳደርም ሆነ የፀጥታ መዋቅሩ ላጋጠማቸው ችግር እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ከለላም መፍትሄ አልሰጧቸውም።  አንዲሁም በጎረቤት ቀበሌዎች ላይ ጥቃቱ የቀጠለ በመሆኑ ተመሳሳይ ችግር በድጋሚ ይደረስብናል የሚል ፍርሀት ውስጥ ከቷቸዋል ፡፡

አዲስ ስታንዳረድ በጉዳዩ ዙርያ ከአቤ ደንጎሮ አስተዳደር ቦሪሳ ሀይሌ እና የወረዳው ሰላም እና ፀጥታ ሀላፊ አዱኛ ዋቆያ መረጃ ለማግኘት ያደረገችው ጥረት አልተሰካም፡፡

ምስራቅ ወለጋ ዞን

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር ጥር ወር መጀመሪያ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከምስራቅ ወለጋ ዞን  ጉቶ ጊዳ ወረዳ ከ128,000 በላይ ሰዎች ‘በአማረኛ ተናጋሪ ፅንፈኛ’ ታጣቂዎች ምክንያት መፈናቀላቸውን አሳውቆ ነበር፡፡ በነዚሁ ታጣቂ ሀይሎች የሚደርሰው ጥቃት ከጊዜ ወደ ግዜ እየጨመረ ሌሎች ምስራቅ ወለጋ የሚገኙ  ወረዳዎችን አዳርሷል፡፡ የሲቡ ስሬ እና ሊሙ ወረዳ ነዋሪዎች ስለደረሰባቸውን መጠነ ሰፊ ጥቃት፣ ስቃይ  እና ዝርፊያ ይናገራሉ፡፡

የሰባት ልጆች አባት የሆነው ካሊፋ ከሶስት ወር በፊት ይኖርበት ከነበረው  የሲቡ ስሬ ወረዳ ዳሎ ካጀማ ቀበሌ በታጣቂዎች ጥቃት ምክንያት ተፈናቀለ፡፡ እንደ ካሊፋ አገላለፅ ታጣቂዎቹ ‘አማርኛ ተናጋሪዎች’ ነበሩ፡፡ “ተድብድበናል፣ ቤታችንም ተቃጥሏል። በዚህም ምክንያት መንደራችንን ትተን በአቅራቢያችን ወዳሉ ከተሞች ሸሽተናል” ብሏል።  ነገርግን የተሰደዱበት ከተማ ለእነርሱ የሚሆን በቂ ምግብ እና መጠለያ እንዳልነበራቸው ይናገራል፡፡ ካሊፋ ጨምሮም የተቀናጀ ድጋፍ እና እርዳታ ባለመኖሩ ምክንያት እሱን የመሰሉ ተፈናቃዩች ሲቡ ሲሬ ውስጥ በሚገኙ ከተሞች ተበትነው ይገኛሉ፡፡

ኢብራሂም ሌላኛው በሲቡ ሲሬ ወረዳ በነበረው ጥቃት የተፈናቀለ ነው፡፡ አሁን ከሚኖርበት ቀዬ  ከ700 ኪ.ሜ  በላይ እርቆ በሀርረጌ ዞን ተጠልሎ ይገኛል፡፡ ካለበት ሆኖ በስልክ ለአዲስ እስታንዳርድ  እንደገለፀው  የወረዳው አስተዳዳሮች  የአካባቢውን ፀጥታ ሳያረጋግጡ ተፈናቃዩችን ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ እያስገደዷቸው ነው፡፡  እንደ  ኢብራሂም ገለፃ  በአካባቢው  የተከሰተው ግጭት በኦሮሞ ነፃነት  ሰራዊት (መንግስተ ሸኔ ብሎ በሚጠራው እና በህዝብ ተወካዩች ምክር በአሸባሪነት የተፈረጀው)  እና በአማረኛ ተናጋሪ ታጣቂዎች መሀከል ነው፡፡ “እንዴት በታጣቂዎች መሀከል ግጭት እየተካሄደ  እያለ ወደ መኖሪያቹ ተመለሱ ይሉናል” በማለት በአግራሞት ጠይቋል፡፡

ከምዕራብ ኦሮሚያ የተፈናቀሉ የኦሮሞ ማህበረሰብ ህጻናት፣ሴቶች እና አረጋውያን በአዳማ፣ጋንዳ ኩርፋ አካባቢ ተጠልለው

ካሊፋ እና ኢብራሂም እንደገለጹት ከሲቡ ሲሬ ወረዳ ብቻ  ከ14,000 በላይ ነዋሪዎች እየተካሄደ ባለው ግጭት ምክንያት  ተፈናቅለዋል።  አክለውም  የአካባቢው አስተዳደሮች የፀጥታው ሁኔታ ሳይስታካከል  ነዋሪዎችን ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ እያስገደዱ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ “እጃችን ላይ ባለው ባህላዊ የጦር መሳሪያ  ራሳችንን እንድንጠብቅ ነግረውናል” ብሏል ካሊፍ፡፡ የዞኑ እና የወረዳው አስተዳዳሮችን  ማብራሪያ  ለማግኘት አዲስ እስታንዳርድ ያደረገችው ጥረት አልተሳካም፡፡

በምስራቅ ወለጋ ሊሙ ወረዳ አማረኛ ተናጋሪ  ታጣቂዎች መጠነሰፊ ጥቃት እና ዝርፊያ እንዳደረሱ የአካባቢው ነዋሩዎች ይናገራሉ።  ሊደርስባቸው በሚችል  የበቀል ጥቃት ፍራቻ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የሊሙ ወረዳ ነዋሪ ለአዲስ እስታንዳርድ በስልክ እንደገለፁት “ሰኞ ጥር 16፤ 2014 በማለዳ አማርኛ ተናጋሪ ታጣቂዎች በመንደራችን  ላይ ጥቃት ፈፀሙ”  ብሏል፡፡  እንደ ነዋሪዎቹ  ምስክርነት ከሆነ ጥቃት ፈፃሚዎቹ  ንብረቶቻቸውን ዘርፈዋል፤ ቤቶቻቸውን አቃጥለዋል እንዲሁም በጥቂት ቤቶች ውስጥ ሰውም አብሮ ተቃጥሏል ፡፡ “በአካባቢያችን ወደ ነበረ ጫካ አመለጥን፡፡ ከ50 በላይ ሰዎች በእሳት ተቃጥለው እንደሞቱ እና ሌሎች ደግሞ በጦር መሳርያ ጥቃት መገደላቸውን ሰምተናል” ሲሉ አስረድተዋል፡፡ የአይን ምስክሩ አክለውም  ታጣቂዎቹ የመጡት በአቅራቢያው ከሚገኘው ከጊዳ አያና አጎራባች አንዶዴ ዲቻ ወረዳ ሳይሆን እንዳልቀረ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

እንደ ሲቡ ሲሬ ወረዳ ነዋሪዎች ሁሉ የሊሙ ወረዳ ነዋሪዎች  ቤታቸው ከሚወዷቸው  ዘመዶቻቸው ጋር ወደ አመድነት ሲቀየር   እና ንብረታቸው ሲዘረፍ የመንግስት በተለይም የአካባቢውን አስተዳዳር  ቸልተኝነትን ወቅሰዋል፡፡  ጥቃት የደረሰባቸው የሊሙ ወረዳ ነዋሪ እንዳሉት  “በጥቃቱ ወቅት ሶስት ልጆቼን አጥቻለሁ፡፡ መሄጃ አጥተን  ጫካ ውስጥ ተደብቀናል” ። ታጣቂዎቹ ከ 30,000 በላይ ከብቶች  ዘርፈዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በአዳማ ጋንዳ ሳቃቃሎ አካባቢ የሚገኙ የአካባቢ ማህበረሰብ ከምዕራብ ኦሮሚያ ለተፈናቀሉ ኦሮሞዎች የኪስ ገንዘብን ጨምሮ ድጋፍ እየሰጡ

ሌላኛው የአይን ምስክር ደግሞ ሊሙ  ወረዳ ውስጥ የምትገኘውን ፊት በቆ የምትባለውን የገጠር መንደር ታጣቂዎች ሙሉ በሙሉ  ወደ አመድነት ለውጠዋታል ብለዋል፡፡ እኘህ እማኝ በሌሎች ምስክሮች እንደተገለፀው ጥቅት ፈፃሚዎቹ አማርኛ ተነጋሪዎች መሆናቸውን ይስማማሉ፡፡ በአካባቢያቸው ከተገለፁት ታጣቂዎች ውጭ የመንግስት የፀጥታ አካላትን  ጨምሮ  ምንም አይነት የታጠቁ ሀይሎች አለመኖራቸውን በአፅኖት አስረድተዋል፡፡ ” ምንም የማያውቁ  ሰላማዊ ነዋሪዎች በጥቃቱ ተጎጂዎች ነበሩ። የገበሬ ቤቶች ተቃጥለዋል።. ሲዘርፉን ዶሮ እንኳን አላስቀሩልንም በለበስነው ልብስ ነው ሸሽተን ያመለጥ ነው” በማለት አግራርተዋል። የሊሙ ወረዳ ተፈናቃዩቹ እንደሚሉት አስቸኳይ የሆነ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ፡፡ “ምግብ እንፈልጋለን፡፡ ከከተሞች በ30 ወይንም 40 ኪሎሜትር እርቀት ላይ ጫካ ውስጥ ስለሆንን ምግብ እንኳን ከነዋሪው ለምነን ማግኘት አንችልም” ብለዋል።

ሙስጠፋ ከድር የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሽን ኮሚሽነር  ለአዲስ እስታንዳርድ እንደገለፁት የኮሚሽኑ ቅርንጫፍ በምስራቅ ወለጋ ዞን  የሲቡ ስሬ እና የ ሊሙ ወረዳ ተፈናቃዩችን ለመርዳት እየሞከረ ነው፡፡ “እስከ አሁን ከ 20,000 ኩንታል በላይ የምግብ እርዳታ ለዞኑ ልከናል፡፡ በተጨማሪም በሲቡ ሲሬ ወረዳ 12,000 እንዲሁም በሊሙ ወረዳ 15,000  ተፈናቃዩችን  መዝግበናል፡፡” እንደ ሙስጠፋ ገለፃ ከሆነ የተፈናቃዩቹ ቁጥር እየተካሄደው ባለው ግጭት ምክንያት ሊጨምር ይችላል፡፡ ባልተረጋጋው  የፀጥታ ችግር ስጋት ምክንያት ምንም አይነት እርዳታ ያለተደረገላቸው ተፈናቃዩች መኖራቸውን  ሀላፊው አልሸሸጉም፡፡

ኮሚሽነር ሙስጠፋ የአካባቢው ፀጥታ ሳይረጋገጥ ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ እየተገደዱ ስላሉ ተፈናቃዩች ጉዳይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ጉዳዩ  የፀጥታ ቢሮ ሀላፊነት በመሆኑ እነርሱን  እንደሚመለከት ገልፀዋል ፡፡ አዲስ እስታንዳርድ ከ አለም አቀፉ  የቀይመስቀል  ኮሚቴ የኢትዩጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ እና የምስራቅ ወለጋ አስተዳዳር  መረጃ ለማግኘት ያደረገችው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም፡፡

ከምዕራብ ኦሮሚያ የተፈናቀሉ የኦሮሞ ማህበረሰብ ተፈናቃዮች በአዳማ ፣ጋንዳ ሳቃቃሎ አካባቢ ተጠልለው የመስጂድ ቅጥር ግቢ ውስጥ የማህበረሰብ ድጋፍ እየተደረገላቸው

እንደ መነሻ
በጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር ያለፈዉ ነሀሴ ላይ አዲስ እስታንዳርድ በሰራው የምርመራ ዘገባ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ባለው ግጭት የአማራ ሚሊሻ ተሳትፎ እንደነበረው ያሳያል። ጥቅምት ላይ በተሰራው ተከታይ ዘገባም ነዋሪዎቹ  የአማራ ታጣቂዎች የሚያደርሱት ጥቃት በክልሉ የሚኖረውን የአማራ ማህበረሰብ ምርኩዝ በማድረግ እንደሆነ ለአዲስ እስታንዳርድ ገልፀዋል። የኢትዩጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በተመሳሳይ ወር ባወጣዉ ማስጠንቀቂያ እራሳቸዉን ለመከላከል በሚል የጦር መሳርያ እንዲታጠቁ ተፈቅዶላቸዋል የተባሉ ነዋሪዎች በሌሎች ባልታጠቁ ነዋሪዎች መሀከል ስለሚኖር የእርስ በእርስ ግጭት ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር። ኮሚሽኑ በመግለጫው ” የእነዚህ ጥቃቶች በተደጋጋሚ መከሰት በኦሮሞ እና በአማራ ማህበረሰብ መካከል ያለውን ውጥረት እና ፍርሀት ሊያባብሰው ይችላል ።”

ምስራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የእርስ በእርስ ግጭት ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግስት ሸኔ ብሎ ከሚጠራው እና በህዝብ ተወካዩች ምክርቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው) እና ከአማራ ታጣቂዎች ጋር የተያያዘ ነው። የዞኑ ነዋሪዎች ባለፈው ህዳር ውስጥ ተከስቶ የነበረውን እና ለቀናት የቆየዉን ግጭት አስመልክቶ ለአዲስ እስታንዳርድ በስልክ እንደገለፁት ” ተደራጅተው የታጠቁ የአማራ ማህበረሰብ አካላት ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግስት ሸኔ ብሎ ከሚጠራው እና በህዝብ ተወካዩች ምክርቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው) ጋር ከነበራቸው በጦር መሳሪያ የታገዘ ግጭት በኋላ ያለታጠቁ ንፁሀን ላይ ተኩስ ከፍተው ነበር።”

ባለፉት ወራቶች ከሲቡ ስሬ እና ሊሙ ወረዳዎች በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ከ ጉቶ ጊዳ፣ ኪራሙ እና ሌሎች ወረዳዎች ተፈናቅለው በምስራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ ተሰራጭተው ይገኛሉ። የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አለማየሁ ተስፋዬ ለኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ በሰጡት ቃለምልልስ።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.