ዜና ፦ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር በደቡብ አፍሪካ አየተካሄደ ያለው የሰላም ንግግር ወደ ተኩስ አቁምና ለተጎዱ ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት እንደሚያመራ ተስፋ እንዳላቸው ገለጹ

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እና የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በኦታዋ ካናዳ። ፎቶ፡ ሙሳ ፋኪ ማሃማት/ትዊተር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18/2015 ዓ.ም፡- የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማሃማት በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት በፌደራል መንግስት ተወካዮችና በትግራይ ባለስልጣናት መሃከል በደቡብ አፍሪካ አየተካሄደ ያለው የሰላም ንግግር ወደ “ለተኩስ አቁምና ለተጎዱ ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት እንደሚያመራ” ተስፋ እንዳላቸው ገለጹ።

ሊቀመንበሩ ይህንን ያሉት በካናዳ(ኦታዋ) ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስር አንቶኒ ብሊንከን ጋር በነበራቸው ስብሰባ ሲሆን ሁለቱም የተወያዩት ጥቅምት 17 ቀን 2015 ላይ ባደረጉት ጉብኝት ነው። እንዲሁም በታህሳስ 4-5 ለሚካሄደው የአፍሪካ-አሜሪካ የመሪዎች ጉባኤ ቅድመ ዝግጅቶች ዙርያ መምከራቸውን ገልፀዋል።

“ከሁለት ቀናት በፊት በኢትዮጵያ ሁለት አካላት መካከል በደቡብ አፍሪካ የሚደረገውን ድርድር አስከፍቻለው፤ ይህ ሂደት አንዲሳካ ጥረት ላደረገችው አሜሪካ ምስጋናችንን አናቀርባለን። ይህም ወደ “ለተኩስ አቁምና የሰብዊ ድጋፍ ተደራሽነትን መንገድ ይጠርጋል” ብለዋል::

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከሊቀመንበሩ ጋር ባደረጉት ምክክር “የአፍሪካ ህብረት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ሁከትና ግጭት ለማስቆም የመሪነት ሚና እየተጫወተ ነው” ብለዋል።

በአፍሪካ ህብረት አየተደረገ ያለው የሰላም ድርድር ጥቅምት 15 አስከ 20 አሁድ ቀን ድረስ ቀጠሮ አንደ ተያዘለት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል አቀባይ ቪንሴንት ማግዌንያ ተናግረዋል ። አስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም እና የሰብአዊ አገልግሎት እንደገና እንዲጀመር” ሊቀመንበሩ ጥቅምት 5 ቀን ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል::

የውጭ ጉዳይ ምኒስትር አንቶኒ ብሊንከንም የሊቀመንበሩን መግለጫ በመደገፍ በዚህ ሳምንት ባወጡት መግለጫ “በአፋጣኝ ተኩስ ማቆም ቅድሚያ ሊሰጠዉ የሚገባ ነገር ነዉ” ያሉ ሲሆን በተጨማሪም “ልዑካን ቡድኑ ለተቸገሩት ሁሉ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረስ፣ ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ በሚወሰዱ እርምጃዎች እና ኤርትራ ከሰሜን ኢትዮጵያ በምትወጣበት ጊዜ ላይ እንዲስማሙ” ጠይቀዋል።

ውይይቱን በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ እና ከቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አንዲሁም የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ ንጉካ ጋር በመሆን ይመሩታል።

የአፍሪካ ህብረት መረጃ አንደሚያመላክተው የኢጋድ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአሜሪካ ተወካዮች በውይይቱ ላይ በታዛቢነት እየተሳተፉ ነው። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.