ዜና: ሶስት በዓለም ሥራ ድርጅት የወጡ ስምምነቶች በሀገራችን ፀድቀው ተግባራዊ እንዲሆኑ ተጠየቀ

ብሩክ አለሙ

አዲስ አበባ ሚያዚያ 10፣ 2014 – የኢትዮጽያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴርሽን (ኢሠማኮ) የአሰሪና ሰራተኛን ጉዳይ በተመለከተ በዓለም ሥራ ድርጅት የወጡ ስምምነቶች ቁጥር 97እና 143፣ ቁጥር 189 እንዲሁም ቁጥር 190 በሀገራችን ፀድቀው ተግባራዊ እንዲሆኑ ጠየቀ፡፡

ኢሠማኮ ተግባራዊ እንዲሆኑ የጠየቀው የፍልሰተኛ ሠራተኞችን የሚመለከቱ ስምምነት ቁጥር 97 እና 143 ፣ የቤት ሠራተኞች ስምምነት ቁጥር 189 እንዲሁም የሥራ ዓለም ጥቃትና ትንኮሳ ስምምነት ቁጥር 190 ሲሆኑ  በሀገራችን ተግባራዊ እንዲሆን ነው የተጠየቀው፡፡

የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ’’ሀገራችን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች ሠራተኞች በመቶ ሺዎቸች የሚቆጠሩ የሀገር ውጭና ሀገር ውስጥ የቤት ሠራተኞች የስራ አለም ጥቃትና ትንኮሳ በስፋት የሚስተዋልባት በመሆኗ እና የሶስቱ የሰራተኛ ጉዳይ ስምምነቶች እጅግ አሳሳቢና ትኩረት የሚሹ በመሆናቸው ስምምነቶቹ እንዲጸድቁና የሀገራችን ህግ አካል  እንዲሆኑ ዘመቻ ጀምረናል’’ ብለዋል፡፡ ህጎቹ ጥቃትና ትንኮሳ ሰለባ የሆኑ ዜጎችን ከሚደርስባቸው ጥቃቶች እና የመብቶች ጥሰቶች መከላከል የሚያስችልና የፆታ እኩልነት የሚያስፍን መልካም የፍልስተኛ ሠረተኞች አስተዳደር እንዲዘረጋ የሚያስችል መሆኑን ኢሠማኮ አስውቋል፡፡

ፕሬዘዳንቱ አክለውም  የስራ እድል ማጣት፣ ድህነት፣ የማያቋሩጡና የተራዘሙ ግጭቶች፣ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል አለመኖር፣የአየር ንብረት መለዋወጥና የተፈጥሮ አደጋ፣ ረሃብና የህዝባ ቁጥር መጨመርና በሌሎች ምክንያቶች ሀገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄድ የሰራተኞት ፍልሰት ምንጭ እንድትሆን አድርጓታል ያሉ  ሲሆን ባለፉት 5 አመታታ ብቻ 839, 000 በላይ ኢትዮጽያውያን ወደ ውጭ የፈለሱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ ሴቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ እስከ 53 ሚሊዮን የሚሆኑ የቤት ሠራተኞች ያሉ ሲሆን ባልተመቻቸ የስራ ሁኔታ የለእረፍት ተገቢ የመድህን ጥበቃ በለሌለባት፣ ያልተመጣጠነ ክፍያ እንዲሁም ለአካልና ለወሲብ ጥቃት መዳረግ፣ ለግዴታ ስራ መዳረግ፣ ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ መሆንና የመሳሰሉት የመብት ጥሰቶች እንደሚደርስባቸው ነው የተገለፀው፡፡

በሀገራችን የቤት ሰራተኞች በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ በአዋጅ ያልተሸፈነ በመሆኑ የህግ ጥበቃ እና ከለላ የላቸውም ያሉት ፕሬዘዳንቱ የሚደርስባቸው ጥቃት ከባድና አሳሳቢ በመሆኑ ተገቢው የህግ ሽፋንና ጥበቃ እንዲደረግላቸው መንግስት፣ ማህበራዊ ሸሪኮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት  ተገቢ የሆነ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አስተዳደር እንዲዘጋጁና የዓለም ስራ ስምምነት  ቁጥር 189 እና 97እና 143 እንዲሁም 190 በሃገራችን ፀድቀው ስራ ላይ እንዲውሉ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን መንግስት ጉዳዩን ተግባራዊ እስኪያደርገው ድረስ ዘመቻዉ እንደሚቀጥልም አሳውቀዋል፡፡

ኮንፌዴሬሽኑ ከሳምንት በፊት ባካሄደው የግማሽ ዓመት ኮንፍረንስ ላይ መንግስት ለኢንዱስትሪ ፓርክ ሰራተኖች የስራ ዋስትና  እና በተከሰተው ኑሮ ውድነት ለይ ዘላቂ መፍትህ እንዲሰጥ መጠየቁም ይታወሳል፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.