ዜና፦ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ ስንታየሁ ቸኮል እስካሁን ፍርድ ቤት አልቀረበም

በማህሌት ፋሲል

ግንቦት 29፣2014 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፦ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፖርቲ (ባልደራስ) የድርጅት  ጉዳይ  ሀላፊ እና የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት ስንታየሁ ቸኮል ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል  በባህር ዳር ከተማ አንደኛ ፖሊስ ጣቢያ በእስር እንደሚገኝ  እና ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ባለቤቱ ውዴ ስንቄ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።

“የፖርቲ አባለት ፊርማ ለማሰባሰብ”  ከመያዙ አንድ ሳምንት በፊት እንደሄደ የተናገሩት ወ/ሮ ውዴ ግንቦት 19 ቀን ታስሯል ብለዋል።  ባለፈው ሳምንት ባለቤታቸውን ጎብኝተው  እንደነበር የተናገሩት  እስካሁን ምርመራም ሆነ ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለአዲስ ስታንዳርድ  አክለው  ተናግረዋል።

“የታሰረበት እስር ቤት ንፅህናው ጥሩ አይደለም።  ውሀ የለም ። ተመላልሼ  መጠይቅ ብፈልግ እንኳን  የታሰረበት ቦታ ሩቅ  በመሆኑ ሁኔታዎችን ከባድ አድርጎብኛል” ሲሉ ተደምጠዋል ።

ስንታየሁ “በአደራ ነው እዚህ ያስቀመጡኝ “ ብሎኛል ያሉት ዉዴ ሶስት ልጆቹ ጭንቀት ላይ እንደሆኑም ጨምረው ተናግረዋል።

ባልደራስ በበኩሉ ግንቦት 27 ቀን፣ 2014 ዓም ባወጣው መግለጫ  ስንታየው ቸኮል ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች  ላለፉት ሁለት አመታት በቃሊቲ እና ቂሊንጦ እስር ቤቶች ታስረው እንደነበር አንስትቶ፣ “ለምን የግፉአን ድምፅ ይሆናሉ?’’ በሚል በህግ ማስከበር ሰበብ በባህር ዳር እንደታሰሩ አስታውቋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.