ዜና፥ በዳውሮ ዞን በዋና የሀይል ማሰራጫ ትራንስፎርመር በተፈጠረ ከባድ ብልሽት መብራት ከተቋረጠ 10 ቀን ሆነው፣ ዞኑ ችግሩን ለመፍታት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16/2015 – በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በሚገኘው የዳውሮ ዞን በዋና የሀይል ማሰራጫ ትራንስፎርመር በተፈጠረ ከባድ ብልሽት መብራት ከተቋረጠ 10 ቀን የሆነው ሲሆን፣ የዞኑ አስተዳደር ችግሩን ለመፍታት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

የዳውሮ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንደገለጸው፣ በዳውሮ ዞን አባ በሚባል አከባቢ በሚገኘው ጊዜያዊ ማሰራጫ ትራንስፎርመር በተፈጠረው ከባድ ብልሽት ከመጋቢት 06/2015 ጀምሮ በዞኑ የተከሰተወ የሀይል መቋረጥ ማህበረሰቡን ለተለያዩ ችግሮች እያዳረገ መሆኑም ተጠቅሷል። ጊዜያዊ መፍትሔ እንዲሆን ከጅማ ዞን ጋር በመተባበር ወደ ዞኑ ሀይል ለማስተላለፍ እየተደረገ ያለው ጥረት ችግር የገጠመው ቢሆንም አሁንም ሙከራ እየተደረገ ነው።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዕጩ ዶ/ር ደስታ ደምሴ በበኩላቸው አሳውቀዋል ለመፍታት ከፍኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ አሳውቀዋል። በአባ ጊዜያዊ የሀይል ማሰራጫ የተበላሸውን ባለ ከፍተኛ Voltage ትራንስፎርመር የሚተካ ሌላ አዲስ ትራንስፎርመር ከአዲስ አበባ ተጭኖ ወደ አባ ጊዜያዊ ማሰራጫ ጉዞ እንደጀመረም አብራርተዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ፣ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታሪኩ አካሉና ለሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ለችግሩ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ ከክልሉ መንግስት፣ ከጅማ ዞን አስተዳደር፣ ከፌዴራል ዋና መስሪያ ቤት የስራ ሀላፊዎችና በፌዴራል ከሚገኙ የዞኑ ተወካዮች ጋር አስፈላጊውን ሁሉ ጥረት እያደረጉ እንዳሉም ተብራርቷል።

ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በተፈጠረው የኤሌክትሪክ ሀይል መቋረጥ ምክንያት በህብረተሰቡ ላይ በደረሰው ዘርፈ ብዙ ጫና ማዘናቸውንም ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል ሲል የዳውሮ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ጨምሮ ገልጿል።

ዋና አስተዳዳሪው በአጭር ቀናት ውስጥ ተስተካክሎ አገለግሎት እንዲሰጥ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ስለሚገኝ መላው የዞኑ ህዝብ በትዕግሥት እንዲጠባበቅ ጥሪ አቅርበዋል። በዞኑ በተደጋጋሚ የሚከሰተው የሀይል መቋረጥ ዘላቂ መፍትሔ እንዲበጅ ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ በመሆን በቀጣይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም አብራርተዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.