ዜና፥ በኦሮምያ እና በሶማሌ ክልሎች በሚገኙ አራት ዞኖች በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ 28 ሰዎች ሲሞቱ አንድ ሚሊየን የሚጠጉ ነዋሪዎች ከፍተረኛ አደጋ ላይ ናቸው፣ተ.መ.ድ.

በህዳር 2015 የዓለም ጤና ድርጅት ቡድን በኢትዮጵያ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር መከላከል ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴ መቀላቀሉን ገልጿል። ፎቶ፡ WHO

አዲስ አበባ፣ጥር 24/ 2015 ዓ.ም፡– በኢትዮጵያ በኮሌራ ወረርሽኝ ሳቢያ 28 ሰዎች ለሞት ሲዳረጉ አንድ ሚሊየን የሚጠጉ ደግሞ ለከፍተኛ አደጋ መጋለጣቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት አስታወቀ። ወረርሽኙ የተከሰተው በኦሮምያ ክልል በባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች በሚገኙ 8 ወረዳዎች እና 66 ቀበሌዎች እንዲሁም በሶማሌ ክልል ሊበን ዞን ሁለት ወረዳዎች መሆኑን የተመድ ሪፖርት አመላክቷል። እስከ ጥር 22 2015 ዓም በኢትዮጵያ ከኮሌራ ጋር በተያያዘ 1055 የሚሆኑ ሰዎች መታመማቸውን ሪፖርት ተደርጎልኛል ያለው ተመድ ከነዚህ ውስጥም 191 የሚሆኑት በመጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች ናቸው ብሏል።

ከጥር ወር መጀመሪያ አንስቶ በጎሮ፣ ነንሰቦ እና ጊርጃ ወረዳዎች የአዳዲስ የኮሌራ ታማሚዎች ቁጥር በ30 በመቶ መጨመሩን የጠቆመው ሪፖርቱ የሟቾቹም እድሜ ከ0 እስክ 14 አመት የእድሜ ክልል የሚሆናቸው ህፃናት ናቸው ብሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በታህሳስ 6 2015 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ሪፖርት በኦሮምያ በባሌ ዞን 5 ወረዳዎች፣ በጊጂ ዞን አንድ ወረዳ እንዲሁም በሶማሌ ክልል በሊበን ዞን 2 ወረዳዎች ወረርሽኙ እየተዛመት ይገኛል ማለቱ ይታወሳል። ይህ ሪፖርት ይፋ ከተደረገ አንድ ወር ከግማሽ በኋላ በተመድ ይፋ የተደረገው ሪፖርት ወረርሽኙ በአደገኛ ሁኔታ በፍጥነት እየተሰራጨ እንደሚገኝ አመላክቷል።

የመጀመሪያው የኮሌራ ወረርሽኝ ሪፖርት የተደረገው ሰኔ 22 2014 በኦሮምያ ደቡባዊ ክፍል በባሌ ዞን ሃረና ቡሉቅ ወረዳ መሆኑ ይታወሳል። የመጀመሪያው የወረርሽኙ ሪፖርት ከተደረገ ጀምሮ ከዞኑ 13 ወረዳዎች መካከል በስድስቱ የተረጋገጠ ሪፖርት ማግኘቱን ተመድ አስታውቋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.