ዜና፡ ፍርድ ቤቱ አቶ አሰፋ ወዳጆ በ60ሺ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ውሳኔ ቢሰጥም የሶዶ ከተማ ፖሊስ ሊለቃቸው እንዳልቻለ ቤተሰቦቻቸው አሳወቁ

በብሩክ አለሙ  @Birukalemu21

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19/2014 ዓ.ም፡- የወላይታን በክልል የመደራጀት ጥያቄ ደጋፊ እና የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት እና የቀድሞ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር አቶ አሰፋ ወዳጆ በትናነትናው እለት ፍርድ ቤት ቀርበው ፍርድ ቤቱ በ60ሺ ብር ዋስ እንዲለቀቁና ውጭ ሆነው ክሱን እንዲከታተሉ ውሳኔ ቢሰጥም የሶዶ ከተማ ፖሊስ ሊለቃቸው ፍቃደኛ አለመሆኑን ባለቤታቸው ምንትዋብ ገብረ ስላሴ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ፡፡

አቶ አሰፋ ወዳጆ ነሐሴ 13 ቀን ፍርድቤት ቀርበው የሶዶ ከተማ አቃቤ ህግ በራሰቸው ማህበራዊ ሚድያዎች እና በስብሰባዎች ላይ በአገር ሰላምና ደህንነት ላይ ችግር ለመፍጠር እና በሀገር ውስጥ ግጭትና ሁከት ለመፍጠር አስቦ በርካታ ተከታይ ባሉት Asefa Oyato Wodajo በሚለው የፌስቡክ  ገጽ ላይ የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃን በተንቀሳቃሽ ምስል አሰራጭቷዋል ሲል ክስ መስርቶባቸዋል፡፡ 

አቶ አሰፋ ነሐሴ 13 ቀን በዋለው ችሎትም “ቤተሰቤ እየተጉላላ ስለሆነ የዋስትና መብት ተከብሮልን ከውጭ ሆኜ ልከራከር” ብለው መጠየቃቸውን ባለቤቱ ምንተዋብ ገብረስላሴ ለአዲስ ስታንዳርደ ገልፀዋል፡፡  ፍርድ ቤቱ በአምስት ቀን ውስጥ ምርመራውን ጨርሶ ለነሐሴ 18 ቀን እንዲቀርብ ሲል ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

በቀጠሮው መሰረት ትናንት የተሰየመው ፍርድ ቤትም አቶ አሰፋ የተከሰሱበት ወንጀል ዋስትና እንደማይስከለክል በመግለፅ በ60ሺ ብር ዋስ እንዲለቀቅ ቢወስንም የሶዶ ከተማ ፖሊስ ግን የፍርድቤቱን ትእዛዝ ባለመቀበል የተቋቋመ ግበረ-ሀይል ስላለ ግበረ-ሀይሉ ሳወስን መልቀቅ ስለማንችል ነገ ተመልሳቹ ኑ ተብለን ሳይለቀቅ ቀርቷል ሲሉ ባለቤቱ ተናግረዋል፡፡ ባለቤታቸው ጨምረውም በተባልነው መሰረት ዛሬ ጠዋት ተመልሰን ስንሄድ በተከሳሹ ላይ ቀረበበት አቤቱታ ስላለ አይለቀቅም ተብለናል ሲል አክለው አስረድተዋል፡፡

በትናንቱ ችሎትም ፍርድ ቤቱ ከሳሹ በክሱ ላይ ምላሽ እንሰዲጥ ለጳጉሜ 3 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

አሰፋ ወዳጆ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለወራት በእስር ካሳለፉት ግለሰቦች መካከል አንዱ ነው።

የወላይታ ዞን ም/ቤት ያቀረበውን የክልል ጥያቄ ተከትሎ ዞኑ በፀጥታ ሃይሎች እና በሰላማዊ ሰዎች መካከል የማያቋርጥ የውጥረት ማዕከል ሆናለች። የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ ሲቪል ሰርቫንቶች እና አክቲቪስቶች ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በፖሊስ ሲታሰሩ እና ሲፈቱ ቆይተዋል።

የወላይታን በክልል የመደራጀት ጥያቄ ደጋፊ እና የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የቀድሞ የዲላ ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበሩት አቶ አሰፋ እሁድ ነሐሴ 1 ቀን 2014 ዓ.ም በሶዶ ከተማ የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አዲስ ስታንዳርድ መዘገቧ ይታወሳል፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.