ዜና፡ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ መንግስት ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ድርድር ሊያደርግ ነው ማለታቸውን ተከትሎ ቡድኑ ድርድሩ እንደሚከናወን አረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16/2015 ዓ.ም፡- ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር በነገው እለት በታንዛኒያ ድርድር እንደሚጀመር መግለፃቸውን ተከትሎ ቡድኑ ባወጣው መግለጫ መንግስት ሶስተኛ አካል ባለበት ድርድር ለማድርግ የቀረቡ ቅድመ ሁኔታዎችን በመቀበሉ ድርድሩ እንደሚጀመር አረጋግጧል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ወዳጅነት አደባባይ ‘ጦርነት ይብቃ፤ ሰላም እናጽና’ በሚል መሪ ሐሳብ ትላንት ማምሻውን በተካሄደ  የምስጋና እና የዕውቅና መርሃ-ግብር ላይ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ድርድር እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡ የወለጋ ሕዝብ እፎይ እንዲል ሁሉም ወገን የበኩሉን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ይህንን ተከትሎ መንግስት ሸኔ ብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ባወጣው መግለጫ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር አለመግባባቶችን በንግግር ለመፍታት የድርድር ሂደቱን መቀበሉን አረጋግጧል።

ነገር ግን ላለፉት አምስት አመታት በኦሮሚያ ክልል ከመንግስት ሃይሎች ጋር ሲዋጋ የቆየው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መንግስት ቡዱኑን ለመጥራት የሚጠቀምበትን “ሸኔ” የሚለውን ስም በጽኑ እንደሚቃወመው ገልጿል።

” የድርጅታችን መጠሪያ፤ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ነው፡፡ ሌላ ማንኛውም ስያሜ ስህተት ከመሆኑም በላይ ማንነታችንን እና ዓላማችንን ለማሳሳት የሚደረግ ሙከራ ነው፤ መንግሥት ይህን አይነት የተሳሳተ መረጃ ከማሰራጨት ሊቆጠብ ይገባል” ሲል የገለፀው ብድኑ መንግሥት ድርጅቱን  ” ሸኔ ” ብሎ ከመጥራት እንዲቆጠብም አሳስቧል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.