ዜና፡ የፌደራል ፖሊስ በወንጀል ተጠርጣሪ የሆኑ ግለሰቦች ያሉበትን የሚያውቅ ጥቆማ እንዲሰጠው ጠየቀ

ምስል- ፌዴራል ፖሊስ

ነሃሴ 16፣ 2014 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፦ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ አንድ አንድ የፌዴራል ፖሊስ የደምብ ልብስ የለበሰ ግለሰብ እና ሌሎች ሶስት ሰዎች በተደራጀ መልኩ አንድ ወርቅ ቤት ገብተው በርካታ ወርቆች ዘርፈው ሲወጡ የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ድረ ገፅ በስፋት መሰራጨቱን ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ ግለሰቦቹ ያሉበትን የሚያውቅ ጥቆማ እንዲሰጠው ጠየቀ፡፡

ተንቀሳቃሽ ምስሉ እንደሚያሳየው የፌዴራል ልብስ የለበሰው ግለሰብ ተባባሪዎቹ ለመዝረፍ እንዲመቻቸው የሽያጭ ባለሙያዋ እንዳታያቸው ሲከልላት ያሳያል፡፡ አንደኛው ግለሰብ በርካታ ወርቆችን ከሰረቀ በኋላ አንድ የፌዴራል ፖሊስ የደምብ ልብስ ከለበሰው ግለሰብ ጋር ተከታትለው ከወጡ በኋላ የተቀሩት ገዢ መስለው ሲያዘናጉ የነበሩት ሁለቱ ሰዎችም አብረው ሲወጡ በተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል ይታያል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ የተጠርጣሪዎችን ምስል በፌስቡክ ገፁ በመለጠፍ ያሉበትን የሚያውቅ ወይም በአጋጣሚ የተመለከተ ጥቆማ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ጥቆማ ለመስጠትም የሚቻልበትን ስልክ ቁጥር ይፋ ያደረገ ሲሆን  በዚህም መሰረት  በስራ ሰዓት ለሚሰጡ ጥቆማዎች 011-5309139  እንዲሁም በማንኛውም ሰዓት ለሚሰጡ ጥቆማዎች 011 -1119475 እና 011-1711012 በመጠቀም ጥቆማውን እንዲሰጡት  ፖሊስ አስታውቋል። በተጨማሪም በነፃ የስልክ መስመር 861 መጠቀምም እንደሚቻል ፖሊስ ገልጿል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.