ዜና፡ የደቡብ ክልል ምክር ቤት የዞን፣ የልዩ ወረዳዎችን መልሶ ለማዋቀር ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቀረበ ፤ በጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ ኮማንድ ፖስት አቋቋመ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ከደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ክፍሉ ዋና ጥያቄ ሲቀበሉ። ምስል- የፌዴሬሽን ምክር ቤት



አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30  ቀን 2014 ዓ.ም ፦ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ክፍሉ ዋና በክልሉ ያሉ አሥር ዞኖች እና ስድስት ወረዳዎች ያሉት በክላስተር በሁለት ተጨማሪ ክልሎች በአዲስ መልክ እንዲዋቀር ጥያቄውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ትናንት አቅርቧል። የዞኖቹ እና ልዩ ወረዳዎቹ ምክር ቤቶች በሐምሌ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ጥያቄውን አጽድቀዋል።

ምክትል አፈ-ጉባዔ አቶ ክፍሉ ለፌዴርሽን ምክር ቤት አገኘሁ ተሻገር እና ለምክር ቤቱ አባላት እንዲሁም ለዞንና ለልዩ ወረዳ ተወካዮች እንደገለፁት የደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች  ምክር ቤት ጥያቄውን “ህገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ” ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ማቅረቡን ገልፀው ክልሉን በአዲስ መልክ በማዋቀር ከአስሩ ዞኖች እና ከስድስት ልዩ ወረዳዎች ውስጥ ሁለት ተጨማሪ ክልላዊ መንግስታትን ለመመስረት የሚጠበቀው ውጤት “የህዝቦችን አብሮነትና አንድነት ያጠናክራል” ብልዋል። በዞኑ እና በልዩ ወረዳዎች በተለያዩ እርከኖች በተካሄደው ሰላማዊ ውይይት ውሳኔ ላይ መድረሱን ከምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከቀድሞ ዘገባዎች በተቃራኒ፣ የጉራጌ ዞን ከዝርዝሩ ጎሏል። የክላስተር ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክር ቤት በደ/ክ/ብ/ብ/ህ/ ም/ቤት ለማስገባት  የተወሰነውን የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የመልሶ ተደራጅቶ ከሌላ ዞኖች ጋር መጣመር  ሆነ የልዬ ወረዳ ለውይይት አልቀረቡም፤ የጉራጌ ዞን የኢኮኖሚ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አለምይርጋ ወልዴ እንዳሉት ከሆነ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ከፌደሬሽን ምክር ቤት በህዳር 17፣ 2011 አም.ያስገባውን የክልልነት ጥያቄ እየተጠባበቀ መሆኑን ገልፅዋል።

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ አቶ ክፍሉ ዋና ባቀረቡት የአደረጃጀት ጥያቄ  መሰረት  ክልልነት የጠየቁት ስድስቱ ዞኖች፡- ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ወላይታ ዞኖች ሲሆኑ አምስቱ ልዩ ወረዳዎች ደግሞ፡- አሌ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ  የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ጥያቄውን ካፀደቀ በኋላ አንድ ክልል ይመሰርታሉ። በተመሳሳይ አራት ዞኖች ሀዲያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ ጠምባሮ እና ስልጤ ዞኖች እና የም ልዩ ወረዳ በአንድ ክልል ይደራጃሉ።  አቶ ክፍሉ  የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ለጥያቄው  “ በሕገ መንግሥቱ ላይ የተመሠረተ” ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቋዋል።

ውይይቶቹን የመሩት የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሆኑት አቶ አገኘው ተሻገር እንዳስታወሱት እነዚህ ጥያቄዎች የ2010 ዓ.ም. ፓለቲካዊ ለውጦችን የሚቀድሙ እንደሆን እና አፋጣኝ ምላሽ በማጣት የግጭቶች መንስኤ መሆናቸውን፣ ከዚህም ባለፈ ለህይወት መጥፋት እና ለንብረት ውድመት ምክንያትም ሆንዋል። ” የኢኮኖሚ እና ፖለቲካዊ ማህበረሰብ ለመገንባት ብሎም በፍትህ የተመሰረተ ልማት ለማረጋገጥ፣ የህዝብ ጥያቄዎች በአፋጣኝ መመለስ አለባቸው። ” የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤው ተናገሩ።

የጉራጌ ዞን ም/ቤት ተወካዮች ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ከአራት አመት በፊት ያቀረቡት የክልልነት ጥያቄ ያለበት ድረጃ እስካሁን የተገለፀም ምንም ነገር የለም። 

አቶ አገኘሁ ተሻገር የ16ቱ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ያቀረቡት ጥያቄዎች በሚመለከታቸው ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የህዝቡን ጥያቄ ሰለሚያንፀባርቁ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቀጣይ ውሳኔ ያሳልፋል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አባል አቶ አለምይርጋ ለዞኑ መገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ የጉራጌ ህዝብ ራሱን የቻለ ክልላዊ የመስተዳድር ጥያቄ  በዞኑ ምክር ቤት ፀድቆ አሁንም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔውን እየተጠባበቀ መሆኑን አስታውቋል። 

ምክር ቤቱ በህዳር 17 ቀን 2010 ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የዞኑ ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ ያሳለፈውን ውሳኔ በመጥቀስ “ምክር ቤቱ የህዝቡን ጥያቄ ከመተግበር ውጪ ሌላ አማራጭ የለውም” ብለዋል፡፡ አክለውም የምክር ቤቱ አባላት ተጠያቂነታቸው ለሕገ መንግሥቱ፣ ለሕዝብና ለኅሊናቸው ብቻ መሆኑን ጠቅሰው አባላቱ የምክር ቤቱን ውሳኔ ከማንም ተጽእኖ ውጪ ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው ብለዋል።

የደህንነት ማስጠንቀቂያዎች እና እገዳዎች

ሐምሌ 26  ቀን የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊና የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ በወልቂጤ ከተማ ባደረጉት የጸጥታ ስብሰባ ላይ የክልሉ የጉራጌ ዞን የመልሶ ማዋቀር ጥያቄን ሽፋን በማድረግ ህገወጥ እና ህገወጥ ተግባራትን እንደማይታገስ አስጠነቅቀዋል። አክለውም ማስጠንቀቂያውን የሚጥስ አካል ላይ የክልሉ ጸጥታ ጥብቅ እርምጃ እንዲወስድ ይገደዳል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ በጉራጌ ዞን የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከክልል አደረጃጀት ጋር ተያይዞ መንግስት ካስቀመጠው አቅጣጫ ውጭ ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ተግባራትን መፈጸም ወይም ይዞ መንቀሳቀስ የማይቻል መሆኑን በትናንትናው እለት አስጠንቅቋል።

ክልከላዎቹን ተግባራዊ ለማድረግ  የኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይል መቋቋሙን የከተማው አስተዳደር አስታውቋል። የከተማው አስተዳደር አብዛኛው ማህበረሰብ መንግስት ያስቀመጠውን አቅጣጫ ተቀብሎ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ቢሆንም አንዳንድ ሠርጎ ገቦች ሊኖሩ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ የእነዚህ አፍራሽ አካላት ሴራ ሰለባ እንዳይሆን እራሱን መጠበቅ እንደሚኖርበት ተገልጿል።

ከሐምሌ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በከተማው ውስጥ ጉራጌ ክልል ወይም ክላስተር አንቀበልም የሚሉ ተሸርቶችን ፣ኮፊያዎችን እና ባነሮችን ይዞ ወይም ለብሶ መውጣት እንደማይቻል ተገልጿል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.