ዜና፡ የዛምቢያ ፖሊስ ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ የተገመቱ 27 አስከሬኖችን በእርሻ አካባቢ “ተጥለው” አገኘ

የሟቾቹ አስከሬኖች የተገኙበት ቦታ ። የፎቶ ክሬዲት፡ mwebantu.com

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 3፣ 2015 ፦ የዛምቢያ ፖሊስ በዋና ከተማዋ ወጣ ብሎ በሚገኝ የእርሻ ቦታ ላይ ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ የተገመቱ የ27 አስከሬኖች “ተጥለው” ማግኘቱን የዛምቢያ ሚዲያዎች ዘገቡ።

የዛምቢያ ፖሊስ ምክትል ቃል አቀባይ ዳኒ ሙዋሌ እንዳሉት 27 አስከሬኖችን በንግዌሬሬ አካባቢ የተገኙት በህዝብ ጥቖማ መሆኑን ገልጸው፣ ፖሊስ ወደ ቦታው በፍጥነት ሲደርስ አንድ ሰው በህይወት ተርፎ መገኘቱን ገልጠዋል።

በረሃብ እና በድካም መሞታቸውን የመጀመሪያ ዘገባዎች ያሳያሉ ሲሉ ዳኒ ሙዋሌ ለሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ገልጠዋል። “ፖሊስ እና ሌሎች የደህንነት አካላት በጉዳዩ ላይ ምርመራ ጀምረዋል” በማለትም አክለዉ ገልዋል።

ሟቾቹ ከ20 እስከ 38 ዓመት የሆናቸው ወንዶች ናቸው። “የመጀመሪያው ምርመራ እንደሚያመለክተው በአጠቃላይ 28 ሰዎች ከ20 እስከ 38 ዓመት የሆኑ ወንዶች በሙሉ በሜንዉድ ንሆሲ፣ በንግዌሬሬ አካባቢ ቺሚኑካ መንገድ ላይ ባልታወቁ ሰዎች ተጥለዋል” በማለት የዛምቢያ ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ገልጧል።

ይህአሳዛኝ ዜና የወጣው የማላዊ ፖሊስ የ25 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ናቸው ያላቸውን አስከሬን የያዘ የጅምላ መቃብር ካገኘ ከሁለት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.