ዜና፡ የትግራይ ባለስልጣናት የኤርትራ ሃይሎች አዲስ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀሙ በማለት ከሰሱ፣ የፌደራል መንግስት ግን የትግራይ ሃይሎችን ጠብ አጭረዋል ብሏል

ኤርትራ ወታደሮች ወታደራዊ ጥቃት የፈጸሙበት አካባቢ አዲ አዋላ በትግራይ ውስጥ ይገኛል።

ግንቦት 23ቀን ፣ 2014 ዓ.ም፣-የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የኤርትራ ሃይሎችን በሳምንቱ መጨረሻ አዲስ ወታደራዊ ጥቃት አድርሰዋል ሲሉ ከሰዋል። መግለጫውን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት አስተያየት የሰጠ ሲሆን በመጀመሪያ በትግራይ ባለስልጣናት ስለተሰጡት ዘገባዎች አላውቅም ብሎ ነበር። ነገር ግን ጥቃቱን የቀሰቀሱት የትግራይ ሃይሎች ናቸው በማለት ወቀሳ አቅርቧል።

የትግራይ ፕሬዝዳንት አማካሪ እና የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም በትዊተር ገፃቸው ላይ እንዳስታወቁት “በኤርትራ 57ኛ እና 21ኛ ክፍለ ጦር በግንቦት 16 ቀን በትግራይ አዲ አወላ ዙሪያ የተከፈተውን ጥቃት የኛ ሃይሎች የተሳካ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ወስደው አክሽፈውታል፣ የኢሳያስ መንግስት ያሰማራው ሃይልም ከጥቅም ውጭ ሆኗል” ብለዋል። አከለውም የኤርትራ ሃይሎች በግንቦት 20 እና 21 ቀን በሽራሮ ላይ ጥቃት ከፍተው ነበር ብለዋል።

ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ፣ ተካሄደ ስለተባለው ውጊያ መረጃው እንደሌላቸው ለቢቢሲ ገልፀው “በኤርትራ በኩል ጦርነት ይከፈታል የሚል እምነት የለንም” በማለት ክሱን ውድቅ አድርገውታል። አክለውም ህወሓቶች ራሳቸው ትንኮሳ ፈጽመው” የሚያሰሙት ክስ ሊሆን ይችላል ብለዋል።

ነገር ግን ሚኒስትሩ ለአል አይን በሰጡት የተለየ መግለጫ ፣ ግጭቱን የፈፀመው ህወሓት እና ሚሊሻዎቹ እንደሆኑ ተናግረው ከሁኔታው ጋር አያይዘው “ብዙ ጉዳት ደርሶባቸዋል” ብለዋል ። ሚኒስቴሩ በተጨማሪም የትግራይ ሃይሎች በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ግጭት ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ገልፀው ህወሀት “ሁለቱንም ሀገራት ወደ ግጭት ለማስገባት ስለሚፈልግ ነው” ሲሉ ለዜና አውታሩ ወቀሳቸውን አቅርበዋል። ቢሆንም ግን ይህ መቼም ቢሆን “አስይስካም” ያሉ ሲሆን የፌደራል መንግስቱም በአካባቢው ያለውን ሁኔታ በተመለከተ መረጃ እንዳለው አስታውቀዋል።

በተቃራኒው የአቶ ጌታቸው መግለጫ የኤርትራ ኃይሎች “ቀጠናውን ወደማያባራ ግጭት እየወሰዱት ነው” ሲሉ የከሰሱ ሲሆን፣ “ይህም ወደ ሰላም ሊደረግ የሚችል ጉዞን የሚያሰናክል” ነው ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ እስካሁን ከኤርትራ በኩል የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.