ዜና፡ የቀድሞ የኢዜማ ሊቀምበር አቶ የሺዋስን ጨምሮ ሰባት አባላት ከፓርቲው በፍቃዳቸው መልቀቃቸውን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የቀድሞ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ)  ሊቀምበር አቶ የሺዋስን ጨምሮ ሰባት አባላት ከፓርቲው በፍቃዳቸው መልቀቃቸውን አስታወቁ፡፡

ከፓርቲው አባልነት መልቀቃቸውን ያስታወቁት ፓርቲውን በስራ አስፈጻሚ ደረጃ ሲመሩ የነበሩት አቶ የሽዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ ኪታባ፣  አቶ ተክሌ በቀለ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ ወ/ሮ ናንሲ ውድነህ፣ አቶ የጁአልጋው ጀመረ እና አቶ ኑሪ ሙደሲር ናቸው፡፡               

ከፓርቲው መለየታቸውን ባሳወቁበት መግለጫቻቸው እንደገለፁት በፓርቲው ውስጥ የተፈጠረው የአቋም ልዩነት ላይ የአካሄድም ልዩነት ተጨምሮበት ትግላችን መስመር ስቶ ከፍተኛ በሆነ በውስጠ ፓርቲ ትግል ውስጥ ተጠልፈን ቆይተናል ብለዋል፡፡

ጨምረውም “የኢትዮጵያ አሁን ሕዝብ በታሪኩ ገጥሞት የማያውቅ እዚህ መከራ ውስጥ ከመግባቱ በፊት መንገዳችንን እንድናስተካክል በፓርቲው ውስጥም በብዙ ታግለናል፡፡ በፓርቲው ጉባኤዎች ሁሉ ሳይቀር ስህተቶች ይታረሙ ይሆናል በማለት የትግሉን መድረክ ለማስፋት ብንሞክርም በተለያዩ ውስጣዊ እና ውጫዊ ምክንያቶች ማሳካት አልተቻለም፡፡ ኢዜማን ጠግኖ ለማዳን ያደረግነው ትግልም ከንቱ ሆኖ ቀርቷል” ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የኢዜማ ከፍተኛ አመራር ሀገርን ለመታደግ ሕዝብንና ፓርቲዎችን አስተባብሮ ከማታገል ይልቅ አገዛዙ እየፈፀመ ላለው ሀገር አቀፍ ግፍ ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል ሲሉ ከሰዋል፡፡

በአባላት ለፓርቲው አመራር የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ተቀብሎ ለጤናማ ውይይት እና ለንግግር ዝግጁ ከመሆን ይልቅ ንቁ አባላቶችን በተለያዩ ፍረጃ ከደንብ እና አሰራር ውጪ ለማሸማቀቅ ሲሞከር በተደጋጋሚ ተመልክተናል ያሉት ግለሰቦቹ በፓርቲው አደረጃጀት ነፃ እና አሳታፊ የሆነ ውይይት ለማድረግ እንዳይከፈት ሆኖ አሁን ባለው አመራር በሩ ተዘግቷል በማለት ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡

ግለሰቦቹ ምንም እንኳን ያለመታከት የውስጥ ትግል ያደረግን ብንሆንም በሂደቱ ለደረሰው ፖለቲካዊ ኪሳራ እኛም ከተወቃሽነት ልናመልጥ እንደማንችል እናውቃለን በማለት ገልፀዋል፡፡

ኢዜማ ከቆመላቸው መሠረታዊ አላማዎች፤ መርሆች እና እሴቶች በመውጣት የገዢውን ቡድን እሴቶች እና አላማዎች እያራመደ ነው ያሉት ግለሰቦቹ ፓርቲውን ማዳን በማይቻልበት ሁኔታ ላይ ተደርሷል ብለዋል። በታሪክ እና በሞራል ተጠያቂ ላለመሆን ፓርቲውን ወደ ሃዲዱ ለመመለስ ያደረግነው ትግል ግቡን ስላልመታ ራሳችንን ከኢዜማ አባልነት ያገለልን መሆኑን እንገልጻለን ሲል በይፋ አስታውቀዋል፡፡ 

ሚያዚያ 11 2015  የኢዜማ  ከፍተኛ አመራሩ አቶ አንዷለም አራጌ ከፓርቲው መልቀቃቸውን አዲስ ስታንዳርድ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ አቶ አንዷለም ኢትዮጵያ በየትኛውም የታሪክ ድርሳን ላይ ከሰፈረው መከራዋ ሁሉ የከፋውን በምታስተናግድበት በዚህ ዘመን ፓርቲው የሚጠበቅበትን ከመወጣት ይልቅ ለገዢው ፓርቲ በማሸብሸብ የአገዛዝ ጡጫ እንዲፈረጥም ማድረጉ ለብዙዎች ፍች ያልተገኘለት ቅዠት ሆኖአል ሲሉ የፓርቲውን አካሄድ ተችተዋል።

ፓርቲው አሁን ያለበትን ሁኔታም ሲገልጹ ከዚህ ሁሉ የሚከፋው ደግሞ ከስሁት መንገዱ ለመመለስ በማይችልበት መዳፍ ውስጥ መጨመቁ ነው ሲሉ ገልጸዋል። የፓርቲውን ችግር ለመፍታት የሁኔታ ትንታኔ በመስራት ሳቀርብ ነበር ያሉት አቶ አንዷለም ለውጥ ሲመጣ አላየሁም ሲሉ አለመተግበሩን ጠቁመዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.