ዜና፡ የሮሃ ቲቪ ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ በጸጥታ ሃይሎች ተያዘች

ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ

ግንቦት 20፣2014 ዓ.ም፣አዲስ አበባ፡-“ሮሃ ሚዲያ ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት የሆነችው ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ ዛሬ ጠዋት በፖሊስ ተይዛ መወሰዷን ባለቤቷ ሮቤል ተስፋዬ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገረ። ሁለት የፌደራል ደንብ የለበሱ እና ሶስት ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድን ዛሬ ጠዋት ከስራ ከባልደረባዋ ቤት “ለጥያቄ ትፈለጊያለሽ” ብለው እንደወሰዷት ተናግሯል። 

እንደባለቤቷ ገለጻ፣ እነዚህ የጸጥታ ኃይሎች ትናንት ከምሽት ክጀምሮ “የነበረችበትን የባልደረባዋን ቤት ከከበቡ በኋላ  የምትጠቀምበትን የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች በሙሉ ወስደዋል” ሲል ተናግሯል። ባለቤቷ አክሎም ከመዓዛ ውጪ ሌላ ሰው እንዳልወሰዱ ገልጾ ጋዜጠኛዋን ወዴት እንደወሰዷትም እንደማያውቅ ተናግሯል። 

ቀደም ሲል በአባይ ሚዲያ ውስጥ ትሰራ የነበረችው ጋዜጠኛ መአዛ በያዝነው አመት ፍርድ ቤት ሳትቀርብ ከአንድ ወር በላይ ታስራ ከቆየች በኋላ ጥር 10 መፈታቷ የሚታወስ ሲሆን  ይህም የመከላከያ ጠበቆቿ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 2ኛ ምድብ ችሎት እስረኛዋን አካልን ነጻ ማውጣት መብቷ እንዲከበር (habeas corpus) መጠየቃቸውም የታወቃል።  ባለፈው ታህሣሥ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ ወደ ሥራ ስትሄድ ሲቪል በለበሱ የጸጥታ ኃይሎች ታስራ ነበር።

የጋዜጠኛዋን እስር ጨምሮ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ የታሰሩትን የታወቁ ጋዜጠኞች፣ ተንታኞች እና የሚዲያ ባለሙያዎች ቁጥር 19 አድርሶታል። እንደ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመጉ) መረጃ በግንቦት 18 እና 19፣ 2014 ዓ.ም ጋዜጠኛ ሳምባቱ አህመድ (ፊንፊኔ የተቀናጀ ብሮድካስቲንግ) እና ጋዜጠኛ በቃሉ አላሚረውን (አልፋ ቲቪ) ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ሰራተኞች በድምሩ 18 ደርሷል።

የኢሰመጉ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር)  “የኢትዮጵያ የሚዲያ ህግ በመገናኛ ብዙኃን ተፈጽሟል ለሚሉ ወንጀሎች ከቅድመ ችሎት መታሰርን በግልፅ የሚከለክል መሆኑን ደግመን እንገልፃለን እና ሁሉም የታሰሩ የሚዲያ ሰራተኞች መፈታት አለባቸው” ብለዋል።

እየተወሰድ ያለው ርምጃ የጀመረው ባለፈው ሳምንት ሲሆን  በሶስት ቀናት ውስጥ ብቻ ደርዘን የሚጠጉ  ጋዜጠኞች እና የሚዲያ አካላትን ለእስር ዳርጓል። በቁጥጥር ስር የማዋል ስራው የተካሄደው በአማራ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችው ባህር ዳር እና አዲስ አበባ ከተማ ነው። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.