ዜና፡ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በመከላከያ ሰራዊት ላይ በመፃፍ ወንጀል እየሰራ ስለሆነ እርምጃ እወስዳለው ማለቱን ጠበቃው ተናገሩ

 በብሩክ አለሙ @Birukalemu21

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14/ 2014፡- የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለአቃቢ ህግ በላከው የመልስ መልስ ጽሁፍ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በተደጋጋሚ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ በተደጋጋሚ እየፃፈ ወንጀል እየሰራ ስለሆነ መከላከያ ሰረዊት እርምጃ እንደሚወስድ የገለፀ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን ለመከልከል ከግምት ውስጥ ያስገባልኝ ማለቱን ጠበቃው አቶ ሄኖክ ለአዲስ ስታንዳርደ ተናገሩ፡፡

አቶ ሄኖክ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እርምጃውን የሚወስደው የጋዜጠኛው ዋስትና ከተፈቀደለት ይሁን በፃፈው ጽሁፍ አለማወቃቸውንም አክለው ገልጸዋል፡፡ 

ሐምሌ 11 ቀን 2014 አቃቢ ህግ ጋዜጠኛ ተመስገን ዋስትና ሊከለከልበት የሚችልበትን መከላከያ ለፍርድ ቤት የመልስ መልስ በፅሁፍ መቅረቡንና ፀሁፉን ትናንት በዋለው ችሎት ላይ እነደተሰጣቸው አቶ ሄኖክ አክሎ ተናግሯል፡፡

ጠበቃ ሄኖክ በዚህ ጉዳይ ላይ “ህጉ ስለማይፈቅድልን እኛ የመልስ ምት መስጠት ባለመቻላችን መከላከያ ሰራዊት እወስዳለሁ ባለው እርምጃ ላይ መልስ ለመስጠትና ጥያቄዎች ማንሳት አልቻልንም” ሲሉ  አስረድተዋል፡፡

በሰኔ 27 ቀን፣ 2014 ዓ.ም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስት ጉዳዩች እና የፀረ ሽብር ችሎት የቀረበው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በተከሰሰበት ሶስት የወንጀል ክሶች በ100,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲወጣ የዋስትና መብት መፈቀዱ ይታወሳል። ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ያቀረበው ዐቃቤ ሕግ፣ የዋስትና መቃወሚያውን  ሰኞ ሃምሌ 11/2014  አቅርቧል፡፡ ዐቃቤ ሕግ ካቀረባቸው የዋስትና መቃወሚያዎች መካከል የሀገር መከላከያ ሠራዊት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የገለፀው ይገኝበታል ሲለ ጠበቃው ገልጸዋል፡፡

የፍትሕ መጽሔት ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዋስትና ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት መዝገብ እያየ መሆኑን ያስታወቀው የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ የወንጀል ይግባኝ ችሎት፣ መዝገቡን አይቶ እንዳልጨረሰ በመጠቆም ውሳኔ ለመስጠት ለሐምሌ 21/2014 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ  ”ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት፣ህዝቡ በመከላከያ ሰራዊት ላይ እንዲሁም በመንግስት ላይ እምነት እንዲያጣ እና እንዲያምፅ በመቀስቀስ” ጠርጥሬዋለሁ ሲል ፖሊስ ሀሙስ ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓም ረፋድ ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወቃል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.