ዜና፡ ኢትዮጵያ ለሳፋሪኮም ኩባንያ የሞባይል ገንዘብ የማገበያየት ፈቃድ መስጠቷ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3/2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ፍቃድ ለሳፋሪኮም የቴሎኮም ኩባንያ መስጠቱ ተገለጸ። ኤም ፒሳ በሚል የሞባይል ስልክ የግብይት አገልግሎት በመስጠት የሚታወቀው ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ በዘርፉ ፈቃድ ያገኘ የመጀመሪያው የውጭ ኩባንያ አድርጎታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሳፋሪኮም ፈቃድ ማግኘቱ አዳዲስ የባንክ አገልግሎቶች በኢትዮጵያ ገበያ ለማስተዋወቅ ሀገሪቱ የያዘችውን አላማ ለመተግበር ቁርጠኛ መሆኑን ያመላክታል ብሏል።

በኢትዮጰያ ያለው የዲጂታል ፋይናንስ አገለግሎት የሞባይል ባንኪንግ፣ የሞባይል ዋሌት፣ የካርድ ባንኪንግን የሚያጠቃልል ሲሆን እንደ ብሔራዊ ባንክ መረጃ ከሆነ አገልግሎቱ በኢትዮጵያ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል።

ባሳለፍነው ታህሳስ ወር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሻሻለውን ብሔራዊ የክፍያ ዘዴ ማጽደቁ ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው ብቸኛ የሀገሪቱ መንግስት ንብረት የሆነው ኢትዮ ቴሎኮም ኩባንያ መሆኑ ይታወቃል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.