ዜና፡ “ትግራይን እንድጎበኝ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ፈቃድ አልሰጡኝም”፡ የኤምኤስኤፍ ስፔን ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ፓውላ ጊል

የኤም ኤሳኤፍ ስፔን ፕሬዚደንት ፓውላ ጊል፡ ምስል MSF

ሐምሌ 19/2014 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፦ የኤምኤስኤፍ (MSF) ስፔን ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ፓውላ ጊል በኢትዮጵያ የነበራቸውን ጉብኝትን አስመልክቶ ለአዲስ ስታንዳርድ በላኩት መግለጫ “በዚህ ሳምንት መጨረሻ የስድስት ቀናት የአዲስ አበባን ጉብኝቴን ሳጠናቅቅ ትግራይን እንድጎበኝ  የኢትዮጵያ ከባለሥልጣናትን  ብጠይቅም ፈቃድ  አልተሰጠኝም” ሲሉ ተናገሩ።  በዚህ ሳምንት መጨረሻ የነበራቸውን የአዲስ አበባ ጉብኝት መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ትግራይ በመሄድ ሊደርጉት ያሰቡትን ጉዞ “በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነው” ሲሉ ገልፀዋል።

ሃላፊዋ በትግራይ ክልል ሶስቱ ባልደረቦቻቸው ከተገደሉ ከአንድ አመት በኋላ፣ ሀዘኑን ቤተሰቦቻቸውን አግኝተው በጉዳዩ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ጋር የምናደርገውን ውይይት እንቀጥላለን የሚል ተስፋ ነበረኝ ያሉ ሲሆን  ይሁን እንጂ ትግራይን እንድጎበኝ ከባለሥልጣናት ፈቃድ አልተሰጠኝም ነበር ብለዋል፡፡

ይህ ማለት በግፍ የተገደሉትን የቴድሮስ እና የዮሐንስን ቤተሰቦች፣ በአሰቃቂ ሁኔታየተገደሉትን ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ባልደረቦቻችንን ህልፈተ ህይወት መዘከር አልችልም ወይም የኤምኤስኤፍ የውስጥ ግምገማ ሂደት ለቤተሰቦቹ ማሳወቅ አልችልም ማለት ነው ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ በላኩት መልዕክት አንስተዋል። 

እኝህ ሃላፊም አክለውም ስለ ክስተቱ ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ጥያቄ ባቀርብም በሦስቱ ሠራተኞቻችን ግድያ ላይ ባደረጉት ምርመራ ዙሪያ ውይይቱን ለመቀጠል ከፌዴራል መንግሥት ተወካዮች ጋር መገናኘት አልቻልኩም ሲሉ ተናግራዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ከአንድ አመት በላይ ስንነጋገር ከቆየን በኋላ፣ በዚያን ወቅት በባልደረቦቻችን ላይ ስለደረሰው ነገር ምንም አይነት ተአማኒነት ያለው መልስ ባለማግኘታችን አዝነናል ያሉ ሲሆን፣ ጉብኝቴ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት ጋር ባለን ግንኙነት ወሳኝ እርምጃ እንዲሆን ታስቦ ነበር፣ እናም በቀጣይ እርምጃዎቻችን ላይ የምናሰላስልበት ጊዜ አሁን ነው። የምንችለውን መንገድ ሁሉ በመጠቀም በባልደረቦቻችን ላይ ለደረሰው ግድያ ተጠያቂነትን ለማምጣት ጥረታችንን እንቀጥላለን ሲሉ አሳስበዋል።

 ከ20 ወራት ግጭት በኋላ፣ አሁን እየጨመረ ከሚሄደው የምግብ ዋስትና እጦት እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ጋር ተዳምሮ፣ ህይወት አድን የህክምና አገልግሎት ሳያገኙ ህዝቦች የሚያጋጥሟቸው አስጨናቂ ሁኔታዎች በጣም ያሳስበኛልም ሲሉ ሃላፊዋ አክለው ለዜና ክፍላችን በላኩት መግለጫ ተናግረዋል። አስ


No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.