ዜና፡ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ በቤላሩስ ድንበር ሞታ ተገኘች

የወጣቷ ኢትዮጵያዊት አስከሬን የተገኘበት አካባቢ።ፎቶ: bialystok.wyborcza

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10/2015 ዓ.ም፡- በሳምንቱ መጨረሻ በፖላንድ እና ቤላሩስ ድንበር አካባቢ የአንድ ኢትዮጵያዊት ሴት አስከሬን በጫካ ውስጥ መገኘቱን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። የፖላንድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ በድንበር አካባቢ ሞተው ከተገኙት ሰዎች ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ አምስተኛዋ መሆኗን ጠቅሰው፣ ሁኔታውን እየመረመሩ መሆኑን ዘገባዎቹ ጨምረው ገልጸዋል

የ28 አመቷ በስም ያልተጠቀሰችው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ እሁድ የካቲት 6 ቀን ከቤላሩስ ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው ቢያሎዊዛ ጫካ ውስጥ ሞታ የተገኘችው መጥፋቷ ከተነገረ ከአንድ ሳምንት በዃላ ነው ።

መገናኛ ብዙሃኖቹ ጨምረው እንደዘገቡት፣ የወጣቷ አስከሬን የተገኘው በአካባቢው የሚሰሩ የሰብአዊ ድንገተኛ አገልግሎት እርዳታ ቡድን አክቲቪስቶች ነው።

የሟቿ ባለቤት እና በወቅቱ አብረው የነበሩ ሌላ ተጏዥ እርዳታ ለመጠየቅ ከሄዱ በኋላ ሟቿ ብቻዋን በጫካ ውስጥ በመቅረቷ እና በመዳከሟ ህይወቷ ሊያልፍ መቻሉን አክቲቪስቶች ተናግረዋል። ምንም አይነት እርዳታም አልደረሳትም። ከእሷ ጋር የነበሩት ሁለቱም በፖላንድ ድንበር ጠባቂዎች ተይዘው ወደ ቤላሩስ ድንበር ተልከዋል ሲሉ ዘገባዎቹ ጨምረው ገልጸዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.