ዜና፡ ተመድ በትግራይ ለረጅም ግዜ ኢንተርኔትን በማቋረጥ እና በሌሎች አካባቢዎችም በተደጋጋሚ በመዝጋት በምትወቀሰው ኢትዮጵያ የበይነ-መረብ ጉባኤ እያስተናገደ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22/2015 ዓ.ም፡- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 17ኛው የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ  በአዲስ አበባ ከህዳር 19-23 ቀን 2015 ዓ.ም “የማይበገር ኢንተርኔት ለዘላ የጋራ ተስፋ” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ እያካሄደ ነው።

በጉባኤው የአሜሪካ የበይነ-መረብ አምባሳደር ናትናኤል ሲ. ፊክንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በትግራይ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት ለረጅም ግዜ በተቋረጠበትና አሁንም ተቋርጦ ባለበት ጉባኤው በኢትዮጵያ እየተካሄደ በመሆኑ ትችት ቢሰነዘርበትም ድርጅቱ ግን ጉባኤውን  እያካሄደ ይገኛል።

እ.ኤ.አ. ህዳር 2020 በፌደራል መንግስት ከአጋር ሃይሎች እና በትግራይ ሃይሎች መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ የትግራይ ክልል በአብዛኛው የኢንተርኔት፣ የቴሌኮሚኒኬሽን እና የባንክ አገልግሎት አልባ ሆኖ ቆይቷል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤውን በኢትዮጵያ ለማስተናገድ መወሰኑ ከዩኤስ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ የደረጃ አባል ሴናተር ጂም ሪሽ ጨምሮ የተለያዩ ትችቶች ቀርቦበታል።

“በአሜሪካ መንግስት በኩል ወደ ጉባኤው ባለስልጣን ለመላክ  መወሰኑ በኢንተርኔት አስተዳደር የከፋ ታሪክ ላለው መንግስት እውቅና መስጠት ነው”

የአሜሪካ መንግስት አንድ ባለስልጣን ወደ መድረኩ ለመላክ ያሳለፈው ውሳኔ “በይነመረብ አስተዳደር የከፋ  ታሪክ ላለውን መንግስት ህጋዊ እውቅና መስጠት ነው” ሲል ጂም ሪሽ ትችቱን አቅርቧል። 

ሌሎች የኢንተርኔት ተደራሽነት መብት ተሟጋቾች ከ6 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የራሷን ህዝቦች የሚጎዱትን ረጅሙን የኢንተርኔት እገዳ በሚካሄድባት ሀገር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢንተርኔት ተደራሽነት ጉባኤ ማካሄዱ አልነበረበትን ሲሉ ትችታቸውን አቅርበዋል።

 ከትግራይ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ በተጨማሪ፣ “የኢንተርኔት መዘጋት መበራከት፣ የሀሳብ ልዩነትን ለመቅረፍ፣ ሃሳብን ለመቆጣጠር እና የመረጃ ፍሰትን በመገደብ” የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትችት ይሰነዘርባቸዋል።

በኢንተርኔት ተጠቃሚነት መብት ዙሪያ የሚሰራ አክሰስ ናውስ ሸትዳዎን ትራከር ኦብትማይዜሽን ፕሮጄክት የተባለ ድርጅት በበኩሉ እአአ ከ2016 ዓም ጀምሮ የኢትዮጰያ ባለስልጣናት በተለያዩ አካባቢዎች እና በአገር አቀፍ ደረጃ ቢያንስ 22 የኢንተርኔት አገልግሎትን ዘግተዋል።

በመላ አገሪቱ፣ ከአማራ እና አፋር ክልሎች በሰሜን፣ እስከ ምዕራብ ኦሮሚያ ከ2018 ጀምሮ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች በሚፈጠሩ የአመጽ ግጭቶች ምክንያት በተደጋጋሚ  የኢንተርኔት መዘጋት ተፈፅሟል  ሆኖም ግን አንድም ጊዜ  ወደነበረበት ለመመለስ ጥረጥ እንዳልተደረገ አክሰስ ዘግቧል።

በደቡብ አፍሪካ እና በኬንያ በተፋላሚ ወገኖች መካከል በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የተፈረመው የሰላም ስምምነት መንግስት የትግራይን መሰረታዊ አገልግሎቶች ወደነበረበት እንዲመለስ የሚያደርግ ቢሆንም የግንኙነት ማቋረጥ እስካሁን አልተነሳም።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.