ዜና፡ በእስር ላይ የነበሩት የኢሰመጉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች በዋስ ተፈተዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 5/ 2015 ዓ.ም፡- በእስር ላይ የነበሩት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ከስምንት ቀናት የእስር ቆይታ በኋላ ትላንት ጥር 4 ቀን 2015 ዓ.ም በገንዘብ ዋስ ተለቀቁ፡፡

ትላንት በዋለው ችሎት የሰበታ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ሦስቱን የምርመራ ባለሙያዎች የ4,000 ብር እንዲሁም የድርጅቱን ሾፌርና ጉዳይ አስፈፃሚ ደግሞ የ3,000 ብር የገንዘብ ዋስ በማስያዝ እንዲፈቱ በወሰነው መሰረት መለቀቃቸውን አሰመጉ አስታውቋል።

የኢሰመጉ ሰራተኛ የሆኑት ዳንኤል ተስፋዬ፣ብዙአየሁ ወንድሙ፣ በረከት ዳንኤል እና ናሆም ሁሴን ታህሳስ 27 ቀን አለም ባንክ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እየተካሄደ ባለው ቤት የማፍረስ እንቅስቃሴን ለማጣራት በሄዱበት ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡

የሰብአዊ መብት መርማሪዎቹን መታሰር ተከትሎ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል  “በአስቸኳይ” እና “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ” በመፍታት እና በእነርሱ ላይ የተመሰረተው ክስ እንዲነሳ ጠይቋል፡፡

“እነዚህ አራት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አንድም ወንጀል አልፈጸሙም። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን በግድ ማፈናቀል ተግባር ላይ መረጃ የማሰባሰብ ስራ ብቻ እያከናወኑ ነበር። መጀመሪያውኑ በፍፁም መታሰር አልነበረባቸውም ፤ በአስቸኳይ እና ያለ ቅድመ ሁኔታ መፈታት አለባቸው። ማንም ሰው ወሳኝ የሆነ የሰብአዊ መብት ስራ በመስራቱ  ወንጀለኛ መባል የለበትም ”ሲሉ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ታይግሪ ቻጉታህ ተናግረዋል።

ኢሰመጉ በሚሰራው የሰብዓዊ መብት ስራዎች  ምክንያት በሰራተኞቹ እና በአባላቶቹ ላይ በሚደረግ ጫና፣ ሀገር ለቆ እንዲሄዱ ማድረግ እንዲሁም ከፍተኛ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እንደ ግድያ፣ እስራትና ማሰቃየት ሲደርስባቸው እንደነበር በሚያወጣቸው  መግለጫዎች ሲገልፅ ቆይቷል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ በመንግስት የሚፈጸሙ ስልታዊ የሆኑ በሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ላይ ተገቢውን ኃላፊነታቸውን በመወጣት ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳይችሉ መጠነ ሰፊ ጫናዎች እየተደረጉባቸው ይገኛሉ ሲል ኢሰመጎ አሳውቋል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.