ዜና፡ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ 45 ተጠርጣሪዎች የሶስት ቀን የረሃብ አድማ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10/ 2015 ዓ.ም፡- በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ 45 የሚሆኑ ጋዜጠኞች፣ የአማራ ምሁራንና ወጣቶች የሶስት ቀን የረሃብ አድማ ማድረጋቸውን ጠበቃ ሰለሞን ገዛሀኝ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፁ፡፡

በአማራ ክልል ልዩ ሀይልን መልሶ ማደራጀት ጋር በተያያዘ በተነሳው ሁከት ጋዜጠኞችን፣ የአማራ ምሁራንና ወጣቶችን ማሰር፣ ማሳደድ በሽብር በሁከት ተጠርጣሪ ማድረግን በመቃወም የረሃብ አድማውን ማድረጋቸውን ጠበቃው ገልፀዋል፡፡

የረሃብ አድማው ከሰኞ ግንቦት 7 አስከ ትላንት ሀሙስ እለት መጠናቀቁን የገለፁት አቶ ሰለሞን ቀጣይ ዙር መች ለማድረግ እንዳሰቡ እናደማያውቁም ገልፀዋል፡፡ ነገር ግን በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ በእስር ላይ የሚገኘው ቴዎድሮስ አስፋው አድማውን እንዳላደረገ ወንድሙ ቢንያም አስፋው ተናሯል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ እነ መስከርም አበራ፣ ዶ/ር አዳነ  እና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ዛሬ ግንቦት 10 ፍርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀን ጠይቋል፡፡ ተከላካይ ጠበቆች ግን ፖሊስ መረጃዎችን በማሰባሰቡ ተጨማሪ 14 ቀን አያስፈልግም ብለው ተከራከረዋል፡፡

“ተጨማሪ ቀን መስጠት ይገባል ወይስ አይገባም፤ የዋስ በብት መስጠት ይገባል ፣ አይገባም” በሚል ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለነገ 4 ሰዓት ቀጠሮ መስጠቱን አቶ ሰለሞን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል፡፡

መስከረም አበራ፣ ዳዊት በጋሻው፣ ቴዎድሮስ አስፋው፣ ጎበዜ ሲሳይን ጨምሮ በርካታ ሰዎች “ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለማፍረስ እና በሽብር ወንጀል” ተጠርጥረው በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.