ዜና፡ በሱዳን የስደተኞች መጠለያ ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ወደ 120 ከፍ ብሏል፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ተቋም

ቱናይባህ የስደተኞች መጠለያ፤ ምስል፡ © የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ተቋም /ታይላን ዳግሲ /2014



አዲስ አበባ፣መስከረም 24/2015ዓ.ም፡- በሁለት የሱዳን የስደተኞች ካምፖች ውስጥ በዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የተጠረጠሩ እና መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር እስከ መስከረም 18 ድረስ120 መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ተቋም አስታወቀ።

በሽታው የተገኘው በምስራቅ ሱዳን ገዳሬፍ ክልል ኣም ራኩባ እና ቱናይባህ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሱዳን ባለስልጣናት ባብዛኛው በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል ያለውን ጦርነት ሸሽተው የሄዱ ኢትዮጵያውያንን ጫምሮ ከ24,000 የሚበልጡ ስደተኞችን በሚያስተናግደው ቱናይባህ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ሶስት ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ መያዛቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ስደተኞቹ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ያለውን ጦርነት ሸሽተው የወጡ የትግራይ ተወላጆች ናቸው።

ከ21,000 በላይ ስደተኞች ባሉበት በኣም ራኩባ መጠለያ ውስጥ ሁለት የተጠረጠሩ ታማሚዎች ተገኝተዋል። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የሱዳን ባለስልጣናት በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ እና የተጠረጠሩ ሰዎችን ለይቶ ማቆያ ክፍል በማስገባት እና ከመጠለያው እንዳይወጡ ማድረጋቸውን ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግቧል።

እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ተቋም ዘገባ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ድረስ በአጠቃላይ በበሽታው የተጠረጠሩ እና መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር 120 ደርሷል።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው በዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት በሽታ ነው። ከእንስሳት ወደ ሰው፣ ከሰው ወደ ሌላ ሰው እና ከአካባቢ ወደ ሰው የሚተላለፍ ኢንፌክሽን በሽታ ነው።

ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የጡንቻ ህመም ፣ የጀርባ ህመም፣ የጉልበት ማነስ እና የሊንፍ እጢ እብጠትን ተከትሎ ከሁለት አስከ ሶስት ሳምንታት ሊቆይ የሚችል ሽፍታ ከቫይረሱ የተለመዱ ምልክቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ሃምሌ 16፣ 2014 ዓ.ም የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴወድሮስ አድሃኖም ገብረእየሱስ የወቅቱ የዝንጀሮ ፈናጣጣ ወረርሽኝ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አለም አቀፍ ስጋት መሆኑን በማወጅ፣ የአለም ጤና ድርጅት ድንገተኛ ኮሚቴ አቃቁሟል፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.