ዜና፡ በመዲናዋ በፈነዳ ቦንብ በ7 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1/ 2015 ዓ.ም፡- ከትላንት በስቲያ ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ/ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ገደማ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ስፍራው ጎሮ አካባቢ ዊኬር በተባለ ግሮሰሪ በረንዳ ላይ በፈነዳ ቦንብ በ7 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ተጎጂዎች ህክምና እየተከታተሉ እንደሚገኙ እና ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ ምርመራው መቀጠሉንም ፖሊስ ጨምሮ ገልጧል፡፡

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር በተሰሩ ስራዎች ወደ አዲስ አበባ የገቡ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያስታወሰው ፖሊስ የከተማዋ ሰላም ውሎ ማደር እንቅልፍ የሚነሳቸው ፀረ-ሰላም ኃይሎችን መኖራቸውን ተገጿል፡፡

አክሎም አነዚህ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ሰላማችንን ለማደፍረስ ወደ ኋላ እንደማይሉ ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ እና አጥፊዎችን በማጋለጥ እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስቧል፡፡ በተለይም አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ለጋራ ደህንነት ሲባል ለጥበቃና ፍተሻ ስራ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትና መረጃዎችን ለመስጠት በአዲስ አበባ ፖሊስ የመረጃ ስልክ ቁጥሮች 011-1-11-01-11 እና በነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወል መረጃ መስጠት እንደሚቻልም የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.