ዜና፡በኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ሃይሎች ስድስት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችን በመዝጋት ሰራተኞቹን በቁጥጥር ስር አዋሉ

በእቴነሽ አበራ

አዲስ አበባ-የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙት ስድስት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በጸጥታ ሃይሎች መዘጋታቸውንና ሰራተኞቻቸው ባልታወቀ ምክንያት መታሰራቸውን የኩባንያው ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ  ነፃነት ተስፋዬ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል። እንደ እርሱ ገለጻ፣ ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሠራተኞች መካከል አንድ አምስተኛው የሚሆኑ ሰራተኞቹ የሚሠሩባቸዉ በመቱ፣ በጊምቢ፣ በጅማ፣ በበደሌ፣ በነቀምትና በአዳማ ከተሞች የሚገኙ ቅርነጫፍ ፅህፊት ቤቶች ግልጽ ባልሆኑ ሁኔታዎች ተዘግተዋል።

 “የጽህፈት ቤቶቹ መዘጋታቸውን ተከትሎ ሰራተኞች ታስረዋል። በአንዳንድ ቅርንጫፎች  ሁሉም ሰራተኞች የታሰሩ ሲሆን ፣ በሌሎች ቅርንጫፎች ግን አመራር ላይ ያሉ ብቻ ናቸው ታሰሩት” ሲል ነፃነት  ተናግሯል።

ከገበሬዎች የተገዙ የግብርና ምርቶች እንዲሁም በነጋዴዎች የተገዙት ምርቶችን ያከማቹ መጋዘኖች ከምርቶቻቸው ተዘግተዋል፡፡ “ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካል ጋር እየተወያየን ነው” ያሉት አቶ ነፃነት፣ ሰራተኞቹ በተለመደው ስራ ላይ ተሰማርተው እንደነበር እና አንዳቸውም ስለ ጉዳዩ እንደማያውቁ ተናግሯል። “የሆነው ነገር ከምርት ገበያ  እውቅና ውጭ ነበር” ብሏል። እነዚህ የተዘጉት ቅርንጫፎቹ በዋናነት ቡና፣ የቅባት እህሎች እና የተለያዩ የጥራጥሬ አዝእርት ግብይት የሚያከናውኑ ሲሆኑ ሁሉም በወደፊት የሀገሪቱ የወጪ ንግድ ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል ሲል ነፃነት አክሏል።

በ2000 ዓ.ም. የተጀመረው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ  ከምርቶች ጀምሮ የተቀናጀ የማከማቻ አሰራርን አቅርቧል “በኢንዱስትሪ ተቀባይነት ያላቸውን ውጤቶች እና ደረጃዎችን መሠረት በማድረግ ለእያንዳንዱ የተሸጠው ምርት በአይነት እስከ መጨረሻው ይደርሳል”።የምርት ገበያው መጋዘኖች ከሚሰጡት አገልግሎቶች መካከል ወደ እያንዳንዱ መጋዘን የሚመጡትን፣የእህል፣የጥራጥሬ፣የዘይት ዘር እና ቡና በምርት ገበያው በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ናሙና ደረጃ መስጠትና፣ ማመዛዘና ማረጋገጥ” ናቸው፡፡

የቤተሰባቸው ስም እንዲጠቀስ ያልፈለጉት በኢትዮጵያ ምርት ገበያ  ጊምቢ  ቅርንጫፍ የላብራቶሪ ቴክኒሻን የሆኑት አቶ ጫላ ለአዲስ ስታንዳርድ በስልክ እንደተናገሩት የፀጥታ ሃይሎች አባላት ሀሙስ ሚያዚያ 20 ቀን ከቀኑ 9 ሰአት አካባቢ ወደ ቢሮአቸው በመምጣት ህንፃውን ዘግተው እና ያለምንም ማብራሪያ ሁሉንም ሰራተኞች በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡ ሁላችንንም ወደ እስር ቤት ወሰዱዉ ካሰሩን በኃላ እኛን ለቀውን ሲሆን ነገር ግን 14 የአስተዳደር አባላት አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ። የምርት ገበያው የጊምቢ ቅርንጫፍ ከ40 በላይ ሰዎችን ቀጥሮ እንደሚሠራ ጫላ ተናግሯል።

ሌላ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የጅማ ከተማ ምንጫችን ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት የፍርድ ቤት ማዘዣ ያልያዙ  የጸጥታ አባላት ሁሉንም ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በመፈተሽ  አምስት የአስተዳደር አባላትን በቁጥጥር ስር አውለዋል። “ከበላይ የመንግስት አካል የተሰጠ ትእዛዝ ነው ቢሉም የትኛው አካል እንደሆነ ግን በስም አልጠቀሱም። ትናንት ጠዋት ወደ ማረሚያ ቤት ባልደረቦቻችንን ለመጠየቅ  ሄድን ነበር፣  ፖሊስ እስካሁን እስር ቤት ከማቆየት በስተቀር ምንም ጥያቄ እንዳልጠየቃቸው ነግረውናል” ብለዋል። ከ35 እስከ 40 የሚደርሱ ሠራተኞች የሚሠሩበት የጅማ ቅርንጫፍ እስካሁን እንደተዘጋ ሲሆን የጸጥታ አስከባሪዎች ግቢውን እየጠበቁ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እነዚህን መጋዝኖችን  አስመልክቶ መግለጫ ያልሰጠ ሲሆን አዲስ ስታንዳርድ ከስድስቱ ከተሞች ፖሊስ አስተያየት ለማግኘት ተደጋጋሚ ያደረገው ሙከራ  አልተሳካም። በጊምቢ የፖሊስ መኮንን ስልኩን ከመዝጋቱ በፊት በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.