ዕለታዊ ዜና፡ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ከለላ ወረዳ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ከባድ ዝናብ በንብረትና በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ


ምስል- ደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን


አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30  ቀን 2014 ዓ.ም፦በደቡብ ወሎ ዞን ከለላ ወረዳ በልጓማ ከተማና ዙሪያው በሚገኙ ቀበሌዎች  ሐምሌ 28/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ከባድ ዝናብ በንብረትና በእንሰሳት ላይ ጉዳት ማድረሱን የደቡብ ወሎ ኮሙኒኬሽን አስታወቀ፡፡

በረዶ ቀላቅሎ  በጣለው ከባድ ዝናብ በቤት እንስሳት፣ በግለሰቦች መኖሪያ ቤቶች፣ በተለያዩ ተክሎችና ቋሚ አትክልቶች፣ የስንዴና የባቄላ ሰብል እንዲሁም ልዩ ልዩ መሰረተ ልማቶች ላይ ከባድ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን  032 ጉምሮ ቀበሌ ከ600 ሄክታር በላይ የስንዴና የባቄላ ሰብል ሙሉ በሙሉ ማውደሙንና በቀጣይም የደረሰው ጉዳት መጠን ተጣርቶ ይፋ እንደሚደረግ ተገልፃል።

የክረምቱ ዝናብ በቀጣይ ቀናትም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንና ኀብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የብሔራዊ ሜትሪዮሎጂ ኤጀንሲ ሰሞኑን ባስተላለፈው መረጃ  አሳስቧል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.