ትኩስ ዜና : የትግራይ ተወላጆች ወታደራዊ ትጥቅና ማሰልጠኛ ካለባቸው አካባቢዎች እንዲርቁ የፌዴራል መንግስት ጥሪ አቀረበ

መቀሌ ፣ የትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና ። ፎቶ፡ ማህደር/ማህበራዊ ሚዲያ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20/2014 ዓ.ም፡- : የትግራይ ተወላጆች ወታደራዊ ትጥቅና ማሰልጠኛ ካለባቸው አካባቢዎች እንዲርቁ የፌዴራል መንግስት ጥሪ አቀረበ ።

መንግስት ዛሬ በሰጠው መግለጫ ለህወሓት “ፀረ ሰላም ዕብሪት ምንጭ የሆኑ ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ እርምጃ እንደሚወስድ” አስታውቋል ።

“መንግሥት እስከ አሁን ድረስ ለሰላም በሩን ክፍት አድርጎ ቢጠባበቅም ጁንታው ጥቃቱን ቀጥሎበታል። በመሆኑም የፌዴራል መንግሥት ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር የገለጸውዝግጁነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለጁንታው ፀረ ሰላም ዕብሪት ምንጭ የሆኑ ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ ርምጃ ይወስዳል።ስለሆነም በትግራይ የምትኖሩ ወገኖቻችን በተለይም የጁንታው ወታደራዊ መሣሪያዎች እናማሠልጠኛዎች ካሉባቸው አካባቢዎች ራሳችሁን እንድታርቁ ይመከራል” በማለት መግለጫው ገልጿል።

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.