ርዕሰ አንቀፅ፡­ ሰላም ያለ ፍትህና ተጠያቂነት፤ ፍትህና ተጠያቂነት ደግሞ ያለ እውነት ሊረጋገጥ አይችልም!

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20/2015 ዓ.ም፡- ለማመን በሚከብድ  ጭካኔና የተሞላው በትግራይ ክልል ተጀምሮ ወደ አማራና አፋር ክልሎች በመስፋፋት ለሁለት አመታት በዘለቀው  ደም አፋሳሽ ጦርነት ምክንያት  በሚሊዮን በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ላይ የደረሰውን አካላዊ፣ ስነልቦናዊ እና አእምሯዊ  ስብራት ለመጠገን  በተኬደው ረጅም ጉዞ መሰረት በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና በህወሓት ባለስልጣናት  መካከል የተፈረመው ጦርነትን የማቆም ስምምነት እና ቀጣይ አቅጣጫ ፍትህ በማረጋገጥ እንዲከናወን ማድረግ ወሳኝ ነው።

ለሁለት ዓመታት በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደው ዘግናኝ ጦርነት በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኘበት አንድ ነገር ቢኖር  በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈፀመ ለማመን የሚከብድ የግፍ ግፍ መሆኑን ነው።   የጦር ወንጀል በስፋት የተፈጸመበት  በሰው ልጆች ላይ ጅምላ ግድያዎች፣ ጅምላ ጾታዊ ጥቃት እና የወሲብ ባርነት በመሳሰሉ የጭካኔ ተግባራት የታጀበ ደም አፋሳሽ ጦርነት ነበር። 

አንዳንድ ዓለም አቀፋዊ  መስፈርቶች ን በመውሰድ ለጦርነቱ ትክክለኛው ስያሜ ከተሰሰጠው “የዘር ማጥፋት ወንጀል” እንደሆነ  አያጠራጥርም። ከዚህም የተነሳ ነበር ጦርነቱን ለማቆም በፌዴራል መንግስት እና በህወሓት መካከል የተደረሰው ስምምነትና የተወሰዱ እርምጃዎች  የተበሰረበት  ዜና መላውን  የዓለም ህብረተሰብ  እፎይታን ያጎናጸፈው።

ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን በርካታ  ስጋቶች አሉ።  ከእነዚህ አሳሳቢ ጉዳዮች  አንዱ ግጭትን ለማቆም በፕሪቶሪያ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተከትሎ ሊኖር ስለሚገባው  ፍትህን እና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ  ጉዳይ  ጋር ተያይዞ በናይሮቢ ከተፈረመው ስምምነትና ቀጣይ የአፈፃፀም ሂደት  ተያይዞ እንዴት ይሆናል የሚለው ዋናው ስጋት ነው።

በተደረሰው የሰላም ስምምነት  አንቀጽ 2 ላይ እንደተገለጸው “ጦርነቱን በዘላቂነት  ለማቋረጥ የሚደግፉ መርሆዎች” ላይ ሁለቱም ወገኖች “መሠረታዊ የሰብአዊ መብቶችን እና የዲሞክራሲያዊ ደንቦችን እና መርሆዎችን እንዲያከብሩ፣ ለሲቪል ዜጎችን ጥበቃ እንዲያደርጉ፣ የአፍሪካ የዲሞክራሲ ቻርተርን እና  ምርጫ እና አስተዳደር ቻርተርን እንዲያከብሩ፣ ተጠያቂነትን እና  ፍትህን በኢፌዲሪ ህገ መንግስት እና በአፍሪካ ህብረት የሽግግር የፍትህ ፖሊሲ ማዕቀፍ መሰረት በማድረግ እንዲተገብሩ በሚል ሰፍሯል።

መሰረታዊ ችግር

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ የልማት አጋሮች በአስከፊው የእልቂት ጦርነት ወቅት የዘረዘሯቸው ሦስት አንኳር ተግባራት ነበሩ፡፡ እነዚህም ጦርነቱ በአስቸኳይ ማቆም፣ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ያለምንም እንቅፋት በተለይም ክልከላና እገዳ ተጥሎበት ወደነበረው ትግራይ ክልል ማቅረብ፣ እንደዚሁም በጦርነቱ ወቅት የተፈጸመውን ግፍና በደል በገለልተኛ የምርመራ ቡድን ተመርምሮ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ማድረግ የሚሉ ናቸው። የኢትዮጵያ መንግስት የፕሪቶሪያው ዘላቂ የጦርነት ማቋረጥ ስምምነት እስኪጸና ድረስ ሶስቱንም ተቃውሟል።

በተጠያቂነት ጉዳይ ላይ በመንግስት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር (OHCHR) መካከል የጋራ ምርመራ ለማድረግ መስማቱን የገለጸው በግማሽ ልብ ነበር። ይሁንና ይህ ጥምር የጋራ የምርመራ ሃይል ስራዎቹን ለመስራት ህጋዊነት እና አጠቃላይነት የሚሉ ሁለት መሠረታዊ ነገሮች ጎድሎት ነበር፡፡

እነዚህን ጉድለቶች መሰረት በማድረግ እና ለተጎጂዎች ተጠያቂነት እና ፍትህ አሰጣጥን የተፈጠረው መወሳሰብ ሊያስከትል የሚችለውን አሉታዊ አንድምታ በመገንዘብ  አለም አቀፉ ማህበረሰብ በታህሳስ ወር 2021 ዓም  በኢትዮጵያ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ኤክስፐርቶች ኮሚሽን አቋቁሟል።

ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን አካል ለማገድ ያልፈነቀለው ድንጋይ ያልበጠሰው ቅጠል የለም፡፡ በአስፈላጊነቱ ላይ ይደረገረ ከነበረው ክርክር አንስቶ እስከ ትክክለኛው አመሰራረት ድረስ በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትም ሆነ በማግባባት እንደዚሁም ኮሚሽነሮቹ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ በማስፈራራት፣ የኮሚሽኑን ሥልጣን እንዲነሳ ለማድረግ ያለ የሌለ አቅሙንና የመንግስት ሃብትን ተጠቅሞ ያላሳለሰ ጥረት አድረጓል።

ይህንን የመንግስት ፍላጎትና ጥረት እውን ለማድረግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያ ኮሚሽኑን ለማገድ የምታደርገውን ጥረት እንዲደግፉ ለማግባባት የመጨረሻ ጥረት አድርገዋል፣ “ቡድኑ በፕሪቶሪያ የተደረሰውን ስምምነት የሚያደናቅፍ እና ተግባራዊ እንዳይሆን ያደርጋል” በማለትም ተናግረዋል። አቶ ደመቀ በግልጽ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ “የገለልተኛ የምርመራ ቡድኑን ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ እንዲሰራ” እንደማትፈቅድ አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ ያለምንም መረጃ ኮሚሽኑ “ፖለቲካዊ ዓላማ ያለው” በስልጣን ላይ ያለውን አካል (መንግስትን) ለመጉዳት ታስቦ የተቋቋመ ነው በሚል መክሷን ቀጥላለች።

በጦርነቱ ወቅት የተፈጸሙ ወንጀሎችን ገለልተኛ እና ሁሉን አቀፍ ምርመራ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት የሚያሳየው ዓይኑን ያፈጠጠ የጥላቻ ተግባር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኮሚሽን ብቻ የተወሰነ አይደለም። በሰኔ ወር 2013 የአፍሪካ የሰብአዊ እና ህዝቦች መብቶች ኮሚሽን  እንዳስታወቀው “በአፍሪካ የሰብአዊ እና ህዝቦች መብቶች ቻርተር አንቀጽ 45 (የአፍሪካ ቻርተር) በአፍሪካ ውስጥ የሰብአዊ መብቶችን የማስጠበቅ ሥልጣንን መሠረት በማድረግ ” የትግራይ ጉዳይ አጣሪ ኮሚሽን ተቋቁሞ “በሐም 2013 ዓም  ሥራውን በይፋይጀምራል።

የኢትዮጵያ መንግስት ውሳኔውን ለማውገዝ ሁለት ቀናት አልፈጀበትም ነበር፡፡ “የአፍሪካ የሰብአዊና የህዝቦች መብት ኮሚሽን “የአጣሪ ኮሚቴ” መቋቋሙን አስመልክቶ ማስታወቁ እና “ሙሉ በሙሉ በብቸኝነት መፈጸሙ እንደሚያሳዝን ገልጸ በመንግስት በኩል የቀረበለት ጥሪ እንፈሌለና ህጋዊ መሰረት እንደማይኖረው አስታውቋል።

ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ገለልተኛ ዓለምአቀፍ የምርመራ ቡድንን እና የአፍሪካ የሰብአዊ እና ህዝቦች መብቶች ኮሚሽን ስራዎችን ለማደናቀፍ የምታደርገው ስፍር ቁጥር የሌላው ሙከራን ወደጎን በመተው   የተባበሩት መንግስታት በቅርቡ የቀድሞ ስልጣናቸውን የተራዘመው ኮሚሽነር ረሚይ ኒጎይ ሉምቡ  የአፍሪካ የሰብአዊ እና ህዝቦች መብቶች ኮሚሽን ሊቀ መንበር በአዲስ አበባ በቅርቡ ባተካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት የምርመራ ስራው በነጻነት በአጣሪ ኮሚሽኑ መከናወኑን ይቀጥላል፡፡

የዓለም ማሕበረሰብ በሁለት ዓመቱ ታይቶ የማይታወቅ አሰቃቂ ጦርነት ወቅት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመውን  አሰቃቅ  ወንጀሎች ገለልተኛ እና አጠቃላይ ምርመራን በማድረግ ረገድ ሁለቱ የምርመራ ቡድኖች  ለሚያከናውኑት ስራ ድጋፉን ማድረግ አለበት።  በተካህደው ደም አፋሳሽ ጦርነት የተፈጸመው የህዝቦች ሰብአዊ መብቶች ጥሰት እውነቱ እንዳይገለጥና  እንዳይወጣ እንዲትከላከል ለኢትዮጵያ ምንም ዓይነት ፍቃድ መሰጠት የለበትም።

የተፈጸመው ወንጀል ምን እንደነበርና የነበረው ስፋትና ክብደት  እውነታው እስካልወጣ ድረስ ፍትህም ሆነ ተጠያቂነት እውን ማድረግ አይቻልም ፍትህና ተጠያቂነት ከሌለ ደግሞ ዘላቂ ሰላም ሊኖር አይችልም። አስ

    No comments

    Sorry, the comment form is closed at this time.