ለመልሶ ማቋቋም የ5 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ተዘጋጀ

አህመድ ሺዴ የገንዘብ ሚኒስተር

አዲስ አበባ፣ታህሳስ18 ፣ 2014-በጦርነትና በግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች መልሶ ማቋቋሚያ የሚውል የአምስት ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት መዘጋጀቱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ገለጹ። መንግስት ከሚመድበው መነሻ በጀት በተጨማሪም ከልማት አጋሮች በተለይም ከአለም ባንክ ለመልሶ ማቋቋሙ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚጠበቅ አቶ አህመድ ገልጸው የመልሶ ማቋቋሙ መርሀ ግብሩ በመንግስት የሚመራ፣ የተቀናጀ፣ በየደረጃው በፕሮግራም ተግባራዊ የሚደረግ፣ ተጠያቂነት ያለውና ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት የሚተጋ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በጦርነቱና በግጭቱ የደረሰውን ጉዳት ለማውቅና በገንዘብ ለመተመን የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት ለማድረግ የሚያስችል የመነሻ ሀሳብ በገንዘብ ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ለመልሶ ማቋቋም ሴክሬታሪያት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የቀረበ ሲሆን የኮሚቴ አባላትም የመልሶ ማቋቋም መርሀግብሩ ከሰሜኑ የሀገራችን ክፍሎች በተጨማሪ በሌሎች ክልሎች በግጭት የተፈናቀሉትንም እንዲያካትት፣ የሀብት አሰባሰብ ድግግሞሽ እንዲወገድና በአንድ ቋት እንዲሰባሰብ፣ ክልሎች ንቁ ተሳትፎ የሚደርጉቡት ምቹ ሁኔታ እንዲመቻች፣ ከሌሎች መሰል ብሄራዊ ኮሚቴዎች ጋር በቅንጅት እንዲሰራና የግሉን ዘርፍና ዲያስፖራውን እንዲያሳትፍ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.