ዜና ፡ በማዕከላዊ ትግራይ ዓብይ ዓዲ ከተማ ከ54 ሺ በላይ ተፈኛቃዮች የሚገኙበት መጠለያ ጣቢያ የምግብና መድኃኒት እጦት መከሱቱ ተገለጸ

በዓብይ ዓዲ መጠለያ ጣቢያ ተጠልልው የሚገኙ ተፈናቃዮች፤ ፎቶ – በስፍራው የሚገኙ የአዲስ ስታንዳርድ ምንጮች

በምህረት ገ/ክርስቶስ @MercyG_kirstos

አዲስ አበባ፣ ጥር 17/2015 ዓ.ም፡- በትግራይ ክልል ለሁለት ዓመታት ሲካሄድ በቆየው ጦርነት ምክንያት በማእከላዊ ትግራይ ዓብይ ዓዲ ከተማ በሚገኝ መጠለያ ጣቢያ ተጠልልው የሚገኙ ከ54,000 በላይ ስደተኞች በምግብና በመድኃኒት አቅርቦት እጥረት ለከፍተኛ ስቃይ መዳረጋቸውን የከተማዋ ባለስልጣን አስታወቁ። 

የዓብይ ዓዲ ከተማ የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ወልዳይ ገ/ማርያም ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት ከመቀሌ 101 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዓብይ ዓዲ ከተማ፣  ከምስራቅ፣ ሰሜን፣ ከማዕከላዊ እና ምዕራብ ትግራይ የተፈናቀሉ እጅግ በርካታ ዜጎችን እያስተናገደች ቢሆንም ተፈናቃዮቹ ለረሃብና ለህክምና ችግር ተጋልጠዋል ብለዋል። 

በትምህርት ቤቶችና በቴክኒክ ኮሌጆች የሰፈሩት ስደተኞቹ በሰብእዊ እርዳታና ህክምና እጦት ለከፍተኛ ችግር እየተዳረጉ መሆኑን የገለጹት እቶ ወልዳይ በከተማዋ አንድ ሆስፒታልና ክሊኒክ ብቻ መኖሩን ጠቅሰው ተፈናቃዮቹ የህክምና እገልግሎት ማግኘት እንዳልቻሉም ብለዋል። 

በጦርነቱ ምክንያት ከነ ስድስት ልጆቻቸው ከቃፍታ ሑመራ ከተማ ወደ ሽረ ከተማ የተፈናቀሉት የ45 አመቷ ወ/ሮ አመተቻእል አይነኩሉ  ነገሮች በመባበሳቸው  ድጋሜ ወደ ዓብይ ዓዲ ተሰደው  በአንድ ቴክኒክ ኮሌጅ መጠለላቸውን ገልጸዋል። 

“ከሶስት ወር በፊት መጥቼ በስደተኛነት ከተመዘገብኩ ጊዜ ገምሮ ምንም እይነት ሰብአዊ እርዳታ ባለማግኘቴ፣ ልጆቼን በየቤቱ በመዞር እየለመንኩኝ ነው ምመግባቸው” ሲሉ ወ/ሮ  አመተቻእል ተናግረዋል።

የተሻለ የሰብእዊ ድጋፍ ፍለጋ ወደ ዓብይ ዓዲ ቢመጡም እስካሁን ምንም ነገር እለማግኘታቸው ነው ለአዲስ ስታንዳርድ የተናገሩት። 

አክለውም “በጦርነቱ ምክንያት ከመጣሁበት ሽራሮ የተውኳቸው ባለቤቴና ትልቁ ልጄ የት እንዳሉ ማወቅ ባለመቻሌ እጅጉን ተጨንቂያለሁ” ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ወልዳይ ገለጻ በአጠቃላይ ከሌላ ስፍራ ተፈናቅለው  በዓብይ ዓዲ የተጠለሉት ዜጎች 79 ሺ 350 የነበሩ ሲሆን የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ እንዲሁም በቂ ሰብዓዊ ርዳታ ባለመኖሩ የተወሰኑ ተፈናቃዮች ወደ ሌሎች የክልሉ ከተሞች ሄደዋል። 

የ76 አመት የእድሜ ባለፀጋ የሆኑት ወለተንሳይ ገብረስላሴ፣ ጦርነቱ ሲቀሰቀስ ከወርዳ ፀገዴ ተፈናቅለው ሽረ ላይ ለአንድ አመት የቆዩ ሲሆን በመጨረሻም ወደ ዓብይ ዓዲ ሊሄዱ ችለዋል። .

“ሽረ ውስጥ ለአንድ አመት ቆይቻለሁ፣ ጦርነቱ ከተባባሰ በኋላ ለስምንት ቀናት በእግር ተጉዤ ወደ ዓብይ ዓዲ ገባሁ፡፡ ወደ ዓብይ ዓዲ ስጓዝ ምንም እይነት ምግብ ባለመኖሩ ቅጠል ነበር የምበላው” ሲሉ ለእዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል። 

“በጦርነቱ ምክንያት ሁሉንም ንብረቶቼን  አጥቻለሁ፣ እራሴን ብቻ ነው ያተረፍኩት፡፡  ከቤተሰቦቼ ጋር ጭምር ነው የተለያየሁት (የት እንዳሉ እላቅም) እዚም መጥቼ መድሃኒት፤ ምግብ እንዲሁም እንክብካቤ የለም” ብለዋል እቶ ወለተንሳይ። 

“የሰብአዊ እርዳታው በወር አንድ ጊዜ ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ስደተኞቹ እየተሰቃዩ ነው” ያሉት እቶ ወልዳይ፣ “ለህዝቡ የምናከፋፍለው የሰብእዊ እርዳታም በቂ እይደለም” ብለዋል።

መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ህዝቡን ለመደገፍ ጥረት ቢያደርጉም እርዳታውን ማግኘት ያልቻሉ ብዙ ሰዎች አሉ ሲል ወልዳይ አክሏል።

የትግራይ ክልል መሪ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል እንደተናገሩት የሰብአዊ እርዳታ ወደ ክልሉ እየገባ ቢሆንም፤ አሁንም  ከ6.5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ አሁንም ከፍተኛ እርዳታ ይፈልጋል ማለታቸውን የክልል ትግራይ ቴሌቭዥን የሳቸውን ንግግር ጠቅሶ ዘግቧል፡፡  በትግራይ ክልል አሁንም በምግብና በመድሃኒት አረጦት ምክንያት ሰው እየሞተ መሆኑንም ገልፀዋል። 

የትግራይ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው  6ኛ የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ  ደብረጽዮን፣ ከሁሉም የትግራይ ማእዘናት የተፈናቀሉ ወገኖች በሰላም ስምምነቱ መሰረት ወደ ቀያቸው ሊመለሱ እንደሚገባ አሳስቧል። “እስካሁን ምንም እይነት እርምጃ አልተወሰደም” ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በታህሳስ ወር መጨረሻ 20 ድርጅቶች ከ100,000 ቶን በላይ ምግብ እና  የህክምና ቁሳቁሶችን ጨምሮ ከአስር ቶን በላይ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ለትግራይ ማድረሳቸውን አስታውቋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት  ባወጣው ሪፖርት መሰረት የሰብአዊ አቅርቦቶች ስርጭትን ወደ ተጎዱ ቦታዎች ለማሰራጨት  “በተቻለ እቅም” በመካሄድ ላይ ነው መሆኑን ጠቁሞ፣ “እንደ ዓዲየት፣ አስገደ፣ ህፃፅ፣ ኒያዲየር፣ ማይ-ፀብሪ/ፀለምቲ እና ዛና ባሉ የሰብአዊ እርዳታዎችን ለማድረስ እስቸጋሪ በሆኑ ቦታዎች  የሰብእዊ እርዳታዎች ለማድረስ ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል፡፡ አንዳንድ አጋሮች በአስገደ እና ዛና እንዲሁም ሽራሮ እና ታህታይ አድያቦን  ጨምሮ በአንዳንድ አካባቢዎች ሰብአዊ እርዳታ እቅርቦት  መጀመራቸውን ሪፖርቱ ገልጧል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.