አዲስ አበባ፣ መስከረም 7/2015 ዓ.ም፡– የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ የሶማሊያ ወታደሮች ከኤርትራ ያልተመለሱበት ምክንያት የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገሪቱ ባለው የፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ሊመልሷቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው ብለዋል። የቪኦኤ ሶማሊ ጋዜጠኛ ሃሩን ማሩፍ እንደዘገበው ኤርትራ የሶማሊያን ሃይል በማሰልጠን ረገድ “ጥሩ ሀሳብ” እንዳላት ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ተናግርዋል።
በአሜሪካ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ኤርትራ 5,000 የሶማሊያ ወታደሮችን ማሰልጠኗን ብቻ ሳይሆን በማስታጠቅም ድጋፍ እያደረገች ነው ብለዋል።
የሶማሊያ መንግስት አሁን በኤርትራ የሰለጠኑ ወታደሮችን ለማስመለስ እየሰራ ነው፣ አሜሪካም ወታደሮቹን በመመለስ እና ከአልሸባብ ጋር ባለው ጦርነት ሶማሊያን እንትደግፍ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ጠይቀዋል። ወታደሮችንም በቅርቡ እናስመልሳቸዋለን በማለት አክለዋል ሲል ጋዜጠኛ ሃሩን ዘግቧል።
በዚህ አመት ግንቦት ወር ላይ የሶማሊያው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ መሀመድ (ፋርማጆ) ለመጀመሪያ ጊዜ 5,000 የሶማሊያ ወታደሮች ባለፈው አመት ወደ ኤርትራ ተልከው ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉን ቢያምኑም የፖለቲካ ውዥንብርን ለመከላከል ወደ ኤርትራ መመለሳቸው ዘግይቷል ብለዋል።
የወቅቱ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በዚህ ክረምት እንደተመረጡ ካደረጉት የመጀመሪያ የባህር ማዶ ጉዞ አንዱ የኤርትራ ጉዞ እና የሶማሊያ ወታደሮች ማሰልጠኛ ካምፕን መጎብኘታቸው ነው። “እዚያ ሄጄ በፎቶው ላይ እንደምትመለከቱት ወንዶቹን አይቻቸዋለሁ። እኔ ወላጅ ነኝ፣ ልጆች ያሉኝ አባት እና አያት ነኝ፣ ስለዚህ የወላጆችን ህመሞች ከልጃቸው ሲሰሙ አውቃለሁ” ሲሉ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በሐምሌ ወር ተናገው “ወደ ሀገራቸው በሰላም ይመለሳሉ” ብለው ቃል ገብተዋል፣ ነገር ግን የሚመለሱበትን የጊዜ ገደብ አልሰጡም።
ፕሬዚዳንቱ አሁን ሶማሊያ በኤርትራ የሚገኙትን ወታደሮቿን ለመመለስ የአሜሪካን ድጋፍ ጠይቀዋል። አስ